Popular Posts

Wednesday, June 20, 2018

በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም

ሰው ከምንም ነገር በላይ በሚያደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሄር አብሮት እንዳለ የሚያደርገው ነገር እግዚአብሄር ያለውን ነገር መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
እግዚአብሔርም፦ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ አለው። እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። ኦሪት ዘጸአት 33፡14-15
ልዩነት የሚያመጣው የእኛ ብዛትና ማነስ አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው የእኛ መበርታትና መድከም አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው የእኛ አዋቂነትና አላዋቂነት አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው የእኛ ዝናና አለመታወቅ አይደለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው እግዚአብሄር ነው፡፡ ልዩነት የሚያመጣው እግዚአብሄር ከእኛ ጋር መሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ የሚሳነው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አያቅተውም፡፡
አሳም፦ አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 1411
ወይም ልዩነት የሚያመጣው ምቹ ስፍራ መሆንህና አለመሆንህ አይደለም፡፡ የእስራኤል ህዝብን እግዚአብሄር ከምድረበዳ ስጋን እንዴት ሊያመጣ ይችላል ብለው አሙት፡፡ እግዚአብሄር በጊዜና በቦታ አይወሰንም፡፡ እግዚአብሄር ግን ጊዜና ቦታ አይገድበውም፡፡ ለእግዚአብሄር ግን የሚሳነው ነገር የለም፡፡
ለነፍሳቸው መብልን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት። እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን? ዓለቱን መታ፤ ውኆችም ወጡ፥ ወንዞችም ጐረፉ፤ እንጀራን መስጠትስ ይችላልን? ለሕዝቡስ ማዕድን ያዘጋጃልን? መዝሙረ ዳዊት 78፡18-20
እግዚአብሄር በሰው ነገር አይታመንም፡፡ እግዚአብሄር በሰው ችሎታ አይደገፈም፡፡ እግዚአብሄር የራሱ ክንድ መድሃኒት ታመጣለታለች፡፡
ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው። ትንቢተ ኢሳይያስ 59፡16
ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ። ትንቢተ ኢሳይያስ 63፡5
በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና፡፡ ሰው እግዚአብሄር የፈለገበትን ነገር እንደሚሰራ ካወቀ ስለብዛት መጨነቅ የለበትም፡፡ እግዚአብሄር ደጋፊ ቲፎዞ አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር በሰው በብዛት አይደገፍም፡፡
ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፦ ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ጭፍራ እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ  146
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #አይሳነውም #ባለቤት #ዝቅታ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #አዋቂ #በጥቂት #በብዙ #ማዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment