Popular Posts

Tuesday, June 12, 2018

ከእረፍት የማገልገል ምስጢር

አገልግሎት ከእረፍት የሚደረግ ታላቅ እድል ነው፡፡ አገልግሎት በነፃነት የምናደርገው ጥቅም ነው፡፡ አገልግሎት መስጠት ፣ መባረክና መጥቀም ነው፡፡ አገልግሎት ከእረፍት የሚደረግ ነገር የነፃነት ስራ ነው፡፡
አገልግሎት ከጭንቀትና ከእረፍት ማጣት የሚደረግ ግዴታ አይደለም፡፡ አገልግሎት የማይቻል ለማድረግ የመሞከር የመላላጥ እንቅስቃሴ አይደለም፡፡ አገልግሎት በእግዚአብሄር እርዳታ የሚደረግ የእግዚአብሄር ስራ ውጤት ነው፡፡ አገልግሎት በእኛ ውስጥ የሚሰራው የእግዚአብሄር ስራ ውጤት ነው፡፡
አገልግሎት ራስ በእግዚአብሄር ረክቶ ሰውን የማርካት እድል ነው፡፡ አገልግሎት ራስ ተወዶ ሰውን የመውደድ ተልእኮ ነው፡፡ አገልግሎት እግዚአብሄር በውስጣችን እንዲሰራ መፍቀድ ነው፡፡ አገልግሎት አብሮን የሚሰራውንብ እግዚአብሄን መተባበር ነው፡፡ አገልግሎት በእኛ ለሚሰራው ለእግዚአብሄር እውቅና መስጠት ነው፡
ማንም በጭንቀትና በመላላጥ እንዲያገለግለው እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡ ማንም በእረፍት ማጣትና በመረበሽ እንዲያገለግለው አግዚአብሄር የእግዚአብሄር ፈቃድ አይደለም፡፡ እየተረበሽንና እየተጨነቅን ከሆነንን ቆም ብለን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ ከአቅማችን በላይ እየተፍጨረጨርን ከሆነ እግዚአብሄር ያለኝን ነው እያደረኩ ያለሁት ወይስ ነገሮችን በራሴ ለማድረግ እየተፍጨረጨርኩ ነው ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡  
እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘው አገልግሎት ከእረፍት የሚወጣ አገልግሎት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘው አግልገሎት ለእግዚአብሄር ዋና ሰራተኝነት እውቅና የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ አገልግሎት በውስጣችን ለሚሰራው ጌታ እውቅና የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ ለእግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ አገልግሎት በውስጣችን በሚደክመው በእግዚአብሄር ፀጋ ላይ የመደገፍ አገልግሎት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ አገልግሎት በእግዚአብሄር የመታመን አግልግሎት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ አገልግሎት እግዚአብሄር የሚሰራውን ስራ የመተባበር አገልግሎት ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚቀበለው አገልግሎት ከእረፍት የሆነ አገልግሎት ነው፡፡  
ከማንነት እውቀት ማገልገል
እግዚአብሄር የሚቀበለው አገልግሎት አርሱን ከማወቅ የሚመጣ አገልግሎት ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሳያውቅ የሚያገለግለው አገልግሎት እግዚአብሄርን ማገልገል አይደለም፡፡ ላኪውን እግዚአብሄርን የማያውቅ ሰው አገልግሎት አገልግሎት አይደለም፡፡ የሚወክለውን የማያውቅ ሰው ውክልና ሙሉ ውክልና አይደለም፡፡ ማን እንደሆነ የማያውቅ ሰው ሌላው ማን እንደሆነ ሊያሳውቅ አይችልም፡፡ ማን እንደሆነ ያልተረዳ ሰው ለሌላው የማንነት እውቀትን ሊሰጥ አይችልም፡፡ አገልግሎታችን ውጤታማ የሚሆነው እርሱን ባወቅነው መጠን ብቻ ነው፡፡ እርሱን ባላወቅነው መጠን እንለፋለን እነጂ ጌታን ማገልገል በፍፁም አንችልም፡፡
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17
ከክብር ማገልገል
እግዚአብሄርን የምናገለግለው ክብራችንን እያጣን አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው የልጅነት ክብራችን ተገፎ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው ከነክብራችን ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለማገልገል ማንም ትምክታችንን ከንቱ እንዲያደርግብን አንፈቅድም፡፡ ማንም ባለጠጋ አደረኩት እንዲል አንፈቅድም፡፡ ከእግዚአብሄር ውጭ ወይም ለእግዚአብሄር ብለው ከሚያደርጉ ሰዎች ውጭ ማንም አገልግሎታችንን እንዲደግፍ አንፈልግም፡፡ በእግዚአብሄር እንጂ በሰው ወጪ ማገልገል እንፈልግም፡፡ እግዚአብሄርን ለማገልገል የሰውን ፊት አናይም፡፡ እግዚአብሄርን ለማገልገል ሰው እንዲያስፈራራን አንፈቅድለትም፡፡ ከእግዚአብሄር ውጭ ስለማገልገላችን ማንም ምስጋናውን እንዲወስድ አንፈቅድም፡፡
ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡15
አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤ አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ። ኦሪት ዘፍጥረት 14፡22-24
ከሙላት ማገልገል
እግዚአብሄር እንድናገለግል የሚፈልገው በተገለገልን መጠን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሌላውን እንድናረካ የሚፈልገው እኛ ራሳችን በረካን መጠን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንድንሰጥ የሚፈልግው በተቀበልን መጠን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንድንሰጥ የሚፈልገው በተሰጠን መጠን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ማየት የሚፈልገው በተሰጠን ነገር ያሳየነውን ታማኝነት ብቻ ነው፡፡
እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡16
ከአቅርቦት ሙላት ማገልገል
እግዚአብሄር የሚፈልገው አገልግሎት በእርሱ ወጭ የሆንነ አገልግሎት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ስናገለግል ለአገልግሎታችን የሚያስፈልገንን ወጭ ሁሉ የሚያሟላው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር የማይደግፈው አገልግሎት የእግዚአብሄር ሳይሆን የሰው አገልግሎት ነው፡፡ እግዚአብሄር አብሮት ሳይቆም እንደምንም ብሎ የሚያገለግል ሰው እግዚአብሄርን እያገለገለ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የሚያገለግል ሰው በከፍታና በዝቅታ ውስጥ ያልፋል ነገር ግን እግዚአብሄርን የሚያገለግል ሰው የእግዚአብሄር እርዳታ እና የሚያስችል ሃይል ፀጋው አይለየውም፡፡ በራሱ ሃይል የሚያገለግል ሰው እግዚአብሄርን አያገለግልም፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡9
ከእረፍት ማገልገል
እግዚአብሄርን የምናገለገልው ተገደን አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የምናገለግለው በፍቅር ነው፡፡ ከፍቅር ውጭ የሚያስገድደን ነገር የለም፡፡ ብናገለግልም ባናገለግልም እንኖራለን፡፡ የምንኖረው ልጅ ስለሆንን እንጂ ስለሰራን ስላልሰራን ወይም ስላገለገልን ስላላገለገልን አይደለም፡፡ የምናገለገልው ለመኖር አይደለም፡፡ የምናገለግለው ስለምንኖር ነው፡፡ የምናገለግልው ላላመቸገር አይደለም፡፡ የምናገለግለው ስለማንቸገር ነው፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
ከመቀመጥ ማገልገል
የምናገለግለው በክርስቶስ ያለን ስፍራ ስለምናውቅ ነው፡፡ የምናገለግለው ከልጅነት ስልጣን መረዳት ነው፡፡ የምናገለግለው ከእግዚአብሄር የልጅነት ክብር ደረጃ ነው፡፡ የምናገለግልው የነገስታት ቤተሰብነት ደረጃ ነው፡፡ የምናገለግለው ከማረፍና ከመቀመጥ ነው፡፡  
በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡6-7
ከትርፍ ማገልገል
የምናገለግለው ከትርፋችን ነው፡፡ የምናገለግለው ከጥማት አይደለም ከእርካታ ነው፡፡ የምናገለግለው ከድካም እይደለም ከብርታት ነው፡፡ የምናገለግለው ከጭንቀት አይደለም ከእረፍት ነው፡፡ ለመባረክ አይደለም የምንባርከው ስለተባረክን ነው የምንባርከው፡፡ ለመዳን አይደለም የምናገለግለው ስለዳንን ነው የምናገለግልው፡፡ ለመለወጥ አይደለም የምናገለግለው ስለተለወጥን ነው የምናገለግለው፡፡  
የምትባረክ ነፍስ ትጠግባለች፥ የረካም እርሱ ደግሞ ይረካል። መጽሐፈ ምሳሌ 1125
በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን። የሉቃስ ወንጌል 1፡74-75
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ክርስቶስ #ጌታ #እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #እውቀት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment