የእግዚአብሔር
ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡16
እግዚአብሄርን
የምናውቀው በቃሉ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምንሰማው በቃሉ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምንራመደው በቃሉ ነው፡፡ እምነት የሚመጣው
በቃሉ ነው፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17
ካለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡ እምነት የሚመጣበት ቃሉ በሙላት
ሲኖርብን እምነታችን ይሞላል፡፡ ቃሉ በህይታችን ሲጎድል እምነታችን ይጎድላል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ
ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6
ፍሬ የምናፈራው በቃሉ ነው፡፡ ቃሉ በህይወታችን ከጎደለ ፍሬያችን ይጎድላል፡፡ ቃሉ
በሙላት ሲኖርብን ፍሬያችን ሙሉ ይሆናል፡፡
አእምሮዋችን የሚታደሰው በቃሉ ነው፡፡ ቃሉ በህይወታችን ሲጎድል የአእምሮዋችን አዲስነት
ይጎድላል፡፡ ቃሉ በሙላት ሲኖርብን አእምሮዋችን በሙላት ይታደሳል፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ
ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2
የእግዚአብሄር ቃል እውቀት በህይወታችን ሲጎድል የእግዚአብሄር ፀጋ በህይወታችን
ይጎድላል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን ሲበዛ የእግዚአብሄር ፀጋ በህይወታችን ይበዛል፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን
ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ የጴጥሮስ
መልእክት 1፡2-3
የእግዚአብሄር ቃል ከህይወታችን ሲጎድል ነፃነታችን ይጎድላል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል
በህይወታችን ሲበዛ ነፃነታችን ይበዛል፡፡
ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 8፡31-32
የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን ሲጎድል ህይወታችን ሙላትን ያጣል፡፡ የእግዚአብሄር
ቃል በሙላት ሲኖርብን ህይወታችን ሙሉ ይሆናል፡፡
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ
ነው ሕይወትም ነው። የዮሐንስ ወንጌል 6፡63
ስለዚህ ነው ለእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን የመጀመሪያውን ስፍራ በመስጠት ፣ መፈለግ
፣ ማንበብና መስማት ማሰላሰል ያለብን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እውቀት #ጥበብ #ሙላት #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ቃል #መልካም
#መታዘዝ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ነፃነት #ሰላም
#ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፀጋ #ሰላም #ልጅ
No comments:
Post a Comment