Popular Posts

Follow by Email

Tuesday, June 26, 2018

የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ?

የእግዚአብሄር አገልጋይ ነውረኛ ጥቅምን የሚጠላ ሰው እንዲሆን መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ አገልጋይ እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘው ነውረኛን ጥቅምን በመጥላት ብቻ ነው፡፡ አገልጋይ በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋው የማይጠፋው ነውረኛን ጥቅምን ባለመውደድ ብቻ ነው፡፡
እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡8-9
ይህን የተናገረው ነቢዩ ሳሙኤል ነበር፡፡ ነቢዩ ሳሙኤል ምን ያህል ህዝቡን በንፅህና ሲያገለግል እንደቆየ ለማሳየት ማን በአላግባብ ጥቅም የሚከሰኝ ሰው አለ ብሎ ይጠይቃል፡፡ ነቢዩ ሳሙኤል ህዝቡን በቅንነት ምን ያህል ሲያገለግል እንደቆየ ፣ ህዝቡን ካለምንም ድብቅ መነሻ ሃሳብ ምንም ጥቅም ሳይፈልግ ሲያገለግል እንደቆየ ይናገራል፡፡
እነሆኝ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ዓይኖቼንስ ለማሳወር ከማን ጋር እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? እኔም እመልስላችኋለሁ። እነርሱም፦ አልሸነገልኸንም፥ ግፍም አላደረግህብንም፥ ከሰውም እጅ ምንም አልወሰድህም አሉ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 12:3-4
ሃዋሪያው ጳውሎስ እንዲሁ ምን ያህል ከሚያገለግላቸው ሰዎች ጥቅምን ፈልጎ እንዳላገለገለ ይናገራል፡፡ ነውረኛ ጥቅም ባለመውደድ ህዝቡን እንዳገለገለ ይመሰክራል፡፡
እንደምታውቁ፥ እያቈላመጥን ከቶ አልተናገርንም፥ እግዚአብሔርም እንደሚመሰክር እያመካኘን በመጐምጀት አልሠራንም፤ የክርስቶስም ሐዋርያት እንደ መሆናችን ልንከብድባችሁ ስንችል፥ ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም። ነገር ግን ሞግዚት የራስዋን ልጆች እንደምትከባከብ፥ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን፤ እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ እናካፍላችሁ ዘንድ በጎ ፈቃዳችን ነበረ፥ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡5-8
ሃዋሪያው ወንጌልን ለመስበክ በማንም ላይ እንዳይከብድ የሚገባውን እንኳን እየተወ በስራ ይደክም እንደነበር ይናገራል፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ ድካማችንና ጥረታችን ትዝ ይላችኋልና፤ ከእናንተ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን እየሠራን፥ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ሰበክን። በእናንተ በምታምኑ ዘንድ በእንዴት ያለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2፡9-10
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #መንፈስ #ጥሪ #ቅንነት #ጥቅም #ወንጌል #ነውረኛ #ረብ #ተጠያቂነት #ንፅህና #መጠበቅ #ምሳሌ #ፍቅር #ምህረት #ይቅርታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ግልፅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልጋይ #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

No comments:

Post a Comment