አንድ ጊዜ በአንድ የክርስትያን መፅሄት ላይ ስለ
አንድ ሴት ታሪክ እያነበብኩ ነበር፡፡ ይህች ሴት ስለትዳርዋ ቃለ መጠይቅ እየተደረገላት ነበር፡፡ በመጠይቁ መካከል ስለትዳርዋ ስትጠየቅ
የመለሰችም መልስ ልቤን ነካኝ፡፡
ይህች ሴት ስትናገር በድሮ ጊዜ ነው ባሌን ያገባሁት
በዚያን ጊዜ ጋብቻ እንዳሁኑ ጊዜ ወንዱና ሴትዋ የሚፈቃቀዱት ተዋውቀውና ተያይተው አልበነረም፡፡ እኔ ባገባሁ ጊዜ የነበረው ስርአት
ትዳር የሚወሰነው በወላጆች ነበር፡፡ ለልጆቻቸው ባልና ሚስት መርጠው የሚወስኑት ወላጆች ናቸው፡፡ ቤተሰብ ስለወሰነና ስላጋባኝ እኔ
የማውቀውን ወንድ አልነበረም ያገባሁት፡፡ ያገባሁት ራሴ መርጬ የወደድኩትን ወንድ አይነበረም፡፡ የወደድኩት ያገባሁትን ወንድ ነበር
ትላለች፡፡
ይህንን ስሰማ ይህ እውነተኛ ፍቅር ነው ልኩኝ፡፡
ይህ የውሳኔ ፍቅር ነው፡፡ ይህ ፍቅር ያዘኝ ለቀቀኝ የሚባል በአፍቃሪው ላይ ያለተመሰረተ ስሜታዊ ፍቅር አይደለም፡፡ ይህ ከስሜት
ያለፈ ፍቅር ነው፡፡
አሁን የወደዱድን ማግባት ይቻላል፡፡ ምንም እንኳን
የወደዱትም ማግባት ደስ ቢልም ነገር ግን ያገቡትን መውደድ ግን ይበልጥ ትህትናን ፣ መረዳትንና ማስተዋልን ይጠይቃል፡፡
ያገቡትን መውደድ ከስሜት ያለፈውን በማስተዋልና
በውሳኔ ላይ የተመሰረተውን ፍቅር ይበልጥ ይገልጠዋል፡፡
ለካ ፍቅር ካለ ፈቃዳችን እንዲይዘንና እንዲለቀን
አያስፈልግም፡፡ ለካ ፍቅር ባይዘንም እኛ ፍቅርን መያዝ እንችላለን፡፡ ለካ በውሳኔ መውደደ እንችላለን፡፡ ለካ መውደድ በፍላጎታችን
ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለካ እውነተኛው ፍቅር በፈለገ ጊዜ የሚይዘንና የሚለቀን ምትሃት አይደለም፡፡ ለካ መውደድ የምንፈልገውን
ሰው መውደድ እንችላለን፡፡ ለካ ለመውደድ የወሰነውን ሰው መውደድ እንችላለን፡፡
ለካ አልኩኝ ያገቡትን መውደድ ይቻላል፡፡
ፍቅር የውሳኔ ጉዳይ ነው የሚባለው ለዚህ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሰጣችሁን ሴት መውደድ ትችላለችሁ፡፡
እግዚአብሄር የሰጣችሁን ወንድ መውደድ ትችላላችሁ፡፡
በራስ አይቻልም ነገር ግን በልባችሁ የፈሰሰው
የእግዚአብሄር ፍቅር ያስችላል፡፡
በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ሮሜ 5፡5
ለካ ሚስታችንን ላለመውድድ ምንም ምክኒያት የለንም፡፡
ለካ ቆይተን ይህችን ሴት አይደለም የወደድኩዋት
ተለውጣለች ማለት አንችልም፡፡ ከፈቀድክ የተለወጠችንውን ሴት መውደድ ትችላለህ፡፡ ውሳኔው ካለህ ተለውጣለች የምትለውን ይህችል አዲስዋን
ሴት መውደድ ትችላለህ፡፡ እግዚአብሄርን ከታዘዝክ መጀመሪያ የወደድኳት ሴት ይህች አይደለችምን የምትለዋን ሴት መውደድ ትችላለህ፡፡
ፍቅር የሚወሰነው በተፈቃሪው ላይ ሳይሆን በአፍቃሪው
ውሳኔ ላይ ነው፡፡ የምንወደው ሰው የምንነቅፍበትን ነገር ዋጥ አድርገን እንድንወደው የሚያስችለን እውነተኛው ፍቅር ነው ፡፡
ይህንን የውሳኔ ፍቅር እንዲሁ የወደደን ጌታ አሳይቶናል፡፡
ካለምክኒያት የወደደን ጌታ ምሳሌ ትቶልናል፡፡ ያለምክኒያት የወደደን ጌታ እኛም እንዲሁ እንድንወድ አስታጥቆናል፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች
ሼር
share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር
#ፍቅር #ምክንያት
#ያለምክንያት #እንዲሁ
#ውሳኔ #የዘላለም
#ታማኝ #ምንጭ
#መውደድ #ስሜት
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ትጋት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#ትዕግስት #መንፈስቅዱስ
#ማስተዋል #ልብ
#መሪ
No comments:
Post a Comment