ልጅን የሚሰጠው እግዚአብሄር በመሆኑ ልጅን መውለድ
እንደመተኛት ቀላል ነው፡፡ ልጅን የሚወልድ ወንድ ከመተኛት ውጭ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም፡፡ ልጅን የሚወልድ ሰው ጎሽ የሚያስብለውና
የሚያሸልመው ምንም ነገር አይሰራም፡፡ ሰው ልጅ ስለወለደ እግዚአብሄር ይሸልመኛል ብሎ ከጠበቀ ተሳስቷል፡፡ እግዚአብሄር ልጅ ስለመወልድ
ማንንም አይሸልምንም፡፡
አባት መሆን ግን እንደ መውለድ ቀላል አይደለም፡፡
ባይወልዱም ለልጆች በአባትነት መንፈስ መመላስ ግን እንደ መውልድ ቀላል አይደለም፡፡ ለልጅ አባት መሆን ግን በእግዚአብሄር ዘንድ
ጎሽ ያስብላል፡፡ አባትነትን ለሚፈልጉ ማነኛውም ልጆች በአባትነት መንፈስ መመላለስ ግን ጎሽ ያሰኛል፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው ልጅ ብቻ አይደለም፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው እግዚአብሄርን የሚፈራ ዘርን ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው የእግዚአብሄርን መልክና አምሳል የሚገልጥን
የእግዚአብሄ ምልካ አምሳል የሚገለጥበትን ልጅ የሚያበረክት አባት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው እርሱን የሚወክለውን አባት ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው አባትነቱን የሚያንፀባረቅን አባት ነው፡፡
እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን?
ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል። ትንቢተ ሚልክያስ 2፡15
እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? በሥጋም በመንፈስም
የእርሱ ናቸው። ለምን አንድ አደረጋቸው? ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለውን2፥15 ወይም ነገር ግን አባታችን በሕይወት እስከ ኖረበት ዘመን
ድረስ ይህን አላደረገም። ምን ይፈልግ ነበረ? ይፈልግ የነበረው ከእግዚአብሔር ዘንድ ልጅ ለማግኘት ነበረ። ዘር ይፈልግ ስለ ነበር
ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ከወጣትነት ሚስታችሁም ጋር ያላችሁን ታማኝነት አታጓድሉ። ትንቢተ ሚልክያስ 2፡15
/አዲሱ መደበኛ ትርጉም/
እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው በእግዚአብሄር መልክና
አምሳል ነው የፈጠረው፡፡ እግዚአብሄር ቤተሰብን ሲፈጥር በእግዚአብሄ መልክና አምሳል ወንድና ሴት አድርጎ ነው የፈጠራቸው፡፡ የእግዚአብሄርን
ሙሉ መልክ የሚገልጠው ወንድና ሴት ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን እንዲወለድ ያደረገው በአባትና በእና የመጨረሻው የቅርብን ግንኘየነት
ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰው በቤተሰብ በአነባትና በእናት እንክብካቤ አነደፊተያደግ ስለፈለገ ልጅ የሚለደው በአባትና በእናይት የመጨረሻው
የቅርን ህግንዑነት ወቅት ነው፡፡
የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር
ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2
እግዚአብሄር የሚፈልገው ልጅ በቤተሰብ የፍቅር
ህብረት መካከል እንዲወለድ ነው፡፡ ልጅ የሚወለደው በወንድና በሴት ጥብቅ ግንኙነት መካከል እንጂ በመተያየት በትንፋሽ ወይም በመነካካት
አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ልጅ በትንፋሽ ወይም በመነካካት ብቻ እንዲወለድ ያላደረገው ይልቁንም በአባትና በእናት ጥብቅ የቤተሰብ
ግንኙነት መካከል እንዲወለድ ያደረገው ልጅ በአባትና በእናት ተኮትኩቶ እንዲያድግ ስለፈለገ ነው፡፡ ልጅ በቤተሰብ ውስጥ በወንድና
በሴት ጥልቅ ግንኙነት እንዲወለድ እግዚአብሄር ያደረገው የእግዚአብሄርን ሙሉ መልክና ምሳሌ እያየና እየተለማመድ እንዲያድግ ነው፡፡
እግዚአብሄር ሰው እንዲወለድና እንዲያድግ የፈለገው
በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ቤተሰብ መካከል ነው፡፡ እግዚአብሄር በአባትና በእናት መካከል ብቻ ልጅ እንዲወለድና እንዲያድግ የፈለገው
የእግዚአብሄርን ሙሉ መልክ የሚለገልጡት ወንድና ሴት ስለሆኑ ነው፡፡
እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር የፈጠረው እንዲበዛ
እንዲባዛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው በቤት ውስጥ በአባትና በእናት መካከል እንዲወለድ እና እንዲያድግ ነው፡፡ እግዚአብሄር
ሰውን የፈጠረው በአባት ተኮትኩቶ እንዲያድግ ነው፡፡
ልጅን ወልደው በአባትነት መንፈስ የማያሳድጉ ሰዎች
በእግዚአብሄር ይገሰፃሉ እንጂ አይኸለሙም፡፡ ነገር ግን ያልወለዱትን ልጅ ጭምር በአባትነት መንፈስ የሚያገለግሉ እግዚአብሄር ይደሰትባቸዋል
ዋጋቸውም ታላቅ ነው፡፡
ስለዚህ ነው ልጅን በእግዚአብሄር መልክና አምሳል
ኮትኩቶ ማሳደግና ሙሉ ሰው ማድረግ እንጂ መውለድ ብቻ ጎሽ የማያስብለው፡፡ ለምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ አባትነትን ማሳየት እንጂ መውለድ
ብቻ ጎሽ እያሰኝም፡፡ ለምናገኛቸውና አባትነታችንን ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ በአባትነት መንፈስ ማገልገል መውደድ መምራት መምከር ማበረታታት
ልጅ እንጂ መውለድ ብቻ በእግዚአብሄር አያሸልምም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
መልካም የአባቶች ቀን!
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ወላጅ
#ፍቅር #አባት
#የአባትነትመንፈስ #መምራት #መጠበቅ #መንከባከብ #እርማት #ጥንካሬ
#ራእይ #ደረጃመስጠት
#ጥላ #ማበረታታት
#አባትነት #ተግሳፅ #መሪ #አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ልብ #ቸርነት
#ትግስት #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment