እርሱ
ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። የማቴዎስ ወንጌል 19፡4-6
ትዳርን የሰራው እግዚአብሄር ነው ፡፡
እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። ኦሪት ዘፍጥረት 2፡18
ባልን ለባልነት ሚስትን ለሚስትነት የሰራቸው እግዚአብሄር
ነው፡፡
አዳምም
ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ኦሪት ዘፍጥረት 2፡20-24
ትዳርን
የሚቃወም የእግዚአብሄርን ስርአት ይቃወማል፡፡
ስለዚህ
ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 13፡2
እግዚአብሄር ክቡር ያለውን ሳያከብር የሚሳካለት
ሰው የለም፡፡
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር
ይፈርድባቸዋል። ወደ ዕብራውያን 13፡4
በእግዚአብሄር እንታመንና እግዚአብሄርን እንታዘዝ፡፡
እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።
የማርቆስ ወንጌል። 10:9
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት
#ጋብቻ #ትዳር
#ባል #ሚስት
#አንድስጋ #እውነት
#ያጣመረውን #አንድስጋ #አይለየው #ትህትና #ትንሳኤ
#ህይወት #ወንጌል
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment