Popular Posts

Follow by Email

Tuesday, June 12, 2018

አባት እግዚአብሔር

ስለ ሰው አባትነት ለመናገር መጀመሪያ የእግዚአብሄርን አባትነት ማየት ያስፈልጋል፡፡ ስለ አባትነት ትክክለኛ ግንዛቤ የምናገኘው የእግዚአብሄርን አባትነት ስናይና ስናጠና ብቻ ነው፡፡ ስለ አባትነት መመዘኛ ለመረዳት የእግዚአብሄርን አባትነት ባህሪ መረዳት ይጠይቃል፡፡ ለማንኛውም አባትነት መመዘኛ የሚሆነው የእግዚአብሄር አባትነት ነው፡፡ ለማንኛውም አባትነት መነሻ የሚሆነው የእግዚአብሄር አባትነት መመዘኛ ነው፡፡  
እግዚአብሄር ኢየሱስን ክርስቶስን እንደአዳኝ ለተቀበሉ ሰዎች ሁሉ አባት ነው፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
እግዚአብሄር ፈፁም አባት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን አባትነት ባህሪያት እንመልከት፡
አባት መልካምን ነገር በመስጠት ይታወቃል፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? የማቴዎስ ወንጌል 7፡7-11
አባት በእንክብካቤው ይታወቃል
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን? እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። የማቴዎስ ወንጌል 7፡26፣31-32
አባት ልጆቹ ከእርሱ ጋር በነፃነት ህብረት እንዲያደርጉ በማድረግ ይታወቃል
አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡15
አባት ለልጆቹ በመራራት ይታወቃል
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ መዝሙረ ዳዊት 103፡13
አባት ልጆቹን በመውደድ ይታወቃል
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። 1 የዮሐንስ መልእክት 3፡1
አባት ለልጆቹ ምህረት በማድረግ ይታወቃል
የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡3
አባት ልጆቹን በማጽፅናናትባ በማበረታታት ይታወቃል
ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። የዮሐንስ ወንጌል 14፡18
ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። የዮሐንስ ወንጌል 14፡15-17
አባት ልጆቹን በመምራት ይታወቃል
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡15፡14
አባት ልጆቹን በመገሰፅ ይታወቃል
እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል። ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን? ወደ ዕብራውያን 12፡5-9
አባት ልጆቹን በመታገስ ይታወቃል
እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? የሉቃስ ወንጌል 18፡7
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ወላጅ #ፍቅር #አባት #እርማት #መገሰፅ #መማር #ማቅረብ #ይቅርታ #መውደድ #እንክብካቤ #ጥበቃ #ጥንካሬ #አባትነት #ተግሳፅ  #መሪ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #አቢይ 

No comments:

Post a Comment