እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡4-5
መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡13
ጥበብ ስለተባለ ብቻ ጥበብ ሁሉ አንድ አይደለም፡፡ በምድር ላይ የሰው ጥበብ አለ የእግዚአብሄር ጥበብ ደግሞ አለ፡፡ የሰው ጥብብና የእግዚአብሄር ጥብብ እጅግ የተለያዩ ጥበቦች ናቸው፡፡
የእግዚአብሄርና የሰው ጥበብ በሚያፈሩዋቸው ፍሬዎች ይታወቃሉ፡፡
ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ። ያዕቆብ 3፡13
ከእግዚአብሄር ዘንድ የሆነው ጥበብ ንፁህ ፥ ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት ፣ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለበት ነው፡፡
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕቆብ 3፡17
የሰው የሆነው ጥበብ መራርነት ቅንአትንና አድመኝነትን ያፈራል፡፡
ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ያዕቆብ 3፡14-16
ከሚሰበኩት ስብከት የተነሳ እምነታቸው በሰው ጥበብ ላይ የሚሆን ሰዎች አሉ፡፡ ከሚሰበኩት ስብከት የተነሳ ደግሞ እምነታቸው በእግዚአብሄር ሃይል ላይ የሚሆን ሰዎች አሉ፡፡ በሚያባብል በጥበብ ቃል የሚሰበኩ ሰዎች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ በመግለጥ የሚሰበኩ ሰዎች አሉ፡፡ የሚያባብል በጥበብ ቃል የተሰበከ ሰው እምነቱ በሰው ጥበብ ላይ ነው የሚሆነው፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ በመግለጥ የሚሰበኩ ሰዎች እምነታቸው የሚሆነው በእግዚአብሄር ሃይል ላይ ነው፡፡
እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡4-5
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #የሰውጥበብ #የእግዚአብሄርጥበብ #በሚያባብል #ተንኮል #መራራ #ቅንዓትና #አድመኛነት #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment