Popular Posts

Follow by Email

Friday, June 22, 2018

ቃሉን ለመታዘዝ የሚጠቅሙ አራቱ ቁልፎች

የእግዚአብሄር ቃል ከመተግበር ውጭ ቃሉን ብአቻ መስማት ምንም ጥቅም አያስገኝም፡፡ ሰውን ወደነኛነት የሚወስደው የእግዚአብሄርን ቃል ማድረግ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ ቢኖር ደስ ይለን ነበር፡፡ ነገር ግን ለነፃነት የእግዚአብሄርን ቃል ማድረግ ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡
ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል። የያዕቆብ መልእክት 1፡25
የእግዚአብሄርን ቃልን እንዴት እንደምንተገብረው ከቃሉ መረዳት ህይወታችንን ወደ እረፍት ያስገባዋል፡፡  
1.      እግዚአብሄር በእኛ ደስታ መሆኑን አለመርሳት

እግዚአብሄር ለእኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ደስተኛ ነው፡፡ እግዚአብሄ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበላችን ደስተኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛን የሚያየን በልጁ በክርስቶስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ይተማመናል፡፡ እግዚአብሄር በእኛ ደስተኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከተሳሳትንና ካሳዘንነው ይናገረናል፡፡ ሰው እግዚአብሄር በእርሱ ደስተኛ እንደሆነ ካወቀ ለተጨማሪ ነገር ይነሳሳል፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። 1 የዮሐንስ መልእክት 3፡1

2.     ያልተረዳነውን ለመፈፀም አለመሞከር  

እንድንተገብራቸው እግዚአብሄር የሚጠብቅብን የእግዚአብሄር ቃል የተረዳነውን ብቻ ነው፡፡ የመፅሃፍ ቅዱስን ትልቅነትና የእግዚአብሄርን ትእዛዝ ብዛት ስንመለከት ይህን ሁሉ ትዛዛት ጠብቀን እግዚአብሄርን ማስደሰት እንችላለን ብለን እናስባለን፡፡ እግዚአብሄርን ማስደሰት ይቻላል፡፡ እግዚአብሄርን ለማስደሰት በተረዳነው መጠን ብቻ እግዚአብሄርን መታዘዝ ይኖርብናል፡፡   
በተረዳነው መጠን እንጂ ከተረዳነው መጠን በላይ እንድንኖር እግዚአብሄር አይጠብቅብንም፡፡ ከተረዳነው መጠን በላይ እንዳልኖርን የሚከሰን ሰይጣን ነው፡፡

እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤ ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡15-16

ከእኛ የሚጠበቀው የተሰጠን ብቻ ነው፡፡

የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤ ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል። የሉቃስ ወንጌል 12፡47-48

3.     ቃሉን ማሰላሰል

ቃን ማሰላሰል ቃሉን ለመፈፀም ሃይልን ይሰጣል፡፡ ቃሉን የሚያሰላስል ሰው ቃሉን ከማያሰላስለው ሰው በላይ ቃሉን ለመፈፀም ሃይልን ያገኛል፡፡

የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡8

4.     ከቃሉ ተቃራኒ ነገር ላለመሰማት መጠንቀቅ

ቃሉ ማሰላሰል ቃሉን ለማድረግ ጉልበት እንደሚሰጠው ሁሉ ከቃሉ የተቃራኒ ነገር ማሰላሰል ፍርሃትን ውስጥ ይከታል፡፡ እንደቃሉ ያለሆነን ነገር መስማትና ማሰብ ቃሉን የመፈፀም አቅማችንን ያዳክማል፡፡ ከቃሉ ሀጋር የነማይሄድን ነገር ማሰላሰል ጥርጣሬን ይጨምራል፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። የማርቆስ ወንጌል 11፡23

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። የያዕቆብ መልእክት 1፡6

በመጨረሻም ስለደረስንበት ደረጃ እግዚአብሄርን ማመስገን ይገባናል፡፡ ሰይጣን የእግዚአብሄርን ቃል ስለመጠበቅ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይፈልጋል፡፡ ለሰይጣን ምንም ብናደርግ በቂ አይደለም፡፡ ለሰይጣን መቼም ብቁ አይደለንም፡፡ ለእግዚአብሄር ግን በቂ ነን፡፡ እግዚአብሄር በተቃራኒው ካልተናገረን ስራችንን ተቀብሎታል፡፡ በደረስንበት ቃሉ የመፈፀም ደረጃ ደስተኛ ልንሆን ያስፈልጋል፡፡

ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡17-18

ደግሞም ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። መጽሐፈ መክብብ 9፡7
እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ። መጽሐፈ መክብብ 9፡7
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍሬያማነት #ፍሬ #ማፍራት #ስኬት #በእኔኑሩ #ቃል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መመዘኛ #መስፈርት #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment