Popular Posts

Wednesday, June 6, 2018

መጣልን የማስተናገድ ጥበብ

የእንግሊዝኛው ሪጄክሽን rejection የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል በአማርኛ ለመተርጎም ቀላል አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህ ቃል መጣል ወይም ውድቅ መደረግ ተቀባይነት አለማግኘት የሚሉትን ቃላት ይወክላል፡፡
ሰው ሲፈጠር ከነኛ ፈቃድ ጋር ነው የተፈጠረው፡፡ ሰው የሚመርጠው ነገር አለ የማይመረጥው ነገር አለ፡፡ እኛም የምንመርጠው ነገር አለ፡፡ የማንመረጥው ነገር አለ፡፡
በህይወቴ መጣልን እንዴት እንደሚያስተናግድ የማያውቅ በህይወትም ሆነ በአገልግሎት የተከናወነለት ሰው አላየሁም፡፡ መጣልን እንዴት እንደምናስተናግደው ማወቅ በህይወት እንዲሳካልንና ያደርጋል፡፡ መጣልን የማስተናገድ በአግባቡ የማስተናገድ ጥበብ በአገልግሎትና በህይወት ለረጅም ጊዜ እንድንዘልቅ የሚያደርግ የህይወት ጥበብ ነው፡፡ መጣልን በአግባቡ የማስተናገድ ክህሎት ከሌለን መጣል በሞላበት በዚህ አለም ውስጥ መቋቋም ስለሚያቅተን እጃችንን እንሰጣለን፡፡ መጣልን ዋጥ አድርገን የማለፍ ችሎታ ከሌለን በህይወት የማይቀሩትና የሚመጡት መጣሎች ሁሉ ይሰብሩናል የተፈጠርንበትን የህይወት አላማችንን ማሳካት ያቅተናል፡፡  
መጣል ያለ ነው
ሁላችንም ነጻ ፈቃድ ያለን ሰዎች ነን፡፡ ያለንን ነጻ ፈቃድ ተጠቅመን የምንመርጣቸውም የማንመርጣቸው ነገሮች አሉ፡፡ መጣልን እንደ እንግዳ ነገር ማየት ሞኝነት ነው፡፡ እኛ ነፃ ፈቃዳችንን ተጠቅመን እሺና እምቢ እንደምንል ሁሉ ሰዎችም ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው እሺና እምቢ የሚሉት ነገር አለ፡፡ ሰዎች ሃሳባችንን ጥያቄያችንን ስጦታችንን አገልግሎታቸንን አለመቀበልና መጣል መብታቸው ነው፡፡
መጣልን መጠበቅ
የምናገረው ሁሉ ተቀባይነት ያገኛል ማለት ጥበብ የጎደለው አስተሳሰብ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንኳን ምርጫ ይሰጣል ፣ ምን እንድትመርጡ እንደሚፈልግ ይመክረታል እንጂ ማንንም አያስገድድም፡፡ ነፃ ፈቃድ ስላችሁ እግዚአብሄር አብኳን ልትመርጡርት የወይም ላትመነርጡር እንደምትችሉ ይጠብቃል፡፡ ሰው የምለው ሁሉ ተቀባይነት ይኑረው ሁሉም ሰው ይቀበለፅ ገሁለመ ሰው ይስማኝ ማለት ትእቢት እንጂ ጥብብ አይደለም፡፡
በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ ዘዳግም 30፡19
መጣልን ከቅርብም መጠበቅ
ብዙ ጊዜ መጣልን የምንጠብቀው ከሩቅ ነው፡፡ እከሌ ሊጥለኝ ይችላል እከሌ ግን ሊጥለኝ አይችልም ብለን ከመጣል ዝርዝር የምናወጣቸው ሰዎች አሉን፡፡ ነገር ግን መፅሃፍ ቅዱስ እናትና አባት እንኳን ሊጥሉ እንደሚችሉ ያስተምራል፡፡
አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ። መዝሙር 27፡10
ቅዱስና ምንም ነቀፋ የሌለበት ኢየሱስን የገዛ ወገኖቹ እንዳልተቀበሉት እንደጣሉት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ እንዴት ያሳዝናል?
የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ዮሃንስ 1፡11
ኢየሱስን ከተቀበሉትም መካከል አንድ ቀን ሃሳባቸውን ለውጠው የሚጥሉት የቅርብ ሰዎች እንደነበሩ በመፅሃፍ ቅዱስ ታሪክ እንመለከታለን፡፡
ስለ ሁላችሁ አልናገርም፤ እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ፦ እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው። ዮሃንስ 13፡18
የእያንዳንዳችን ምርጫ አንደ ዋጋ አሰጣጣችን ይለያል፡፡ እኛ የሁሉንም ሰዎች ምርጫ ልናሟላ አንችልም፡፡ ለምሳሌ ሰዎች ለመንፈሳዊ ነገር ይበልጥ ዋጋ የሚሰጡ ከሆነ ምድራዊውን ነገርን ይጥላሉ፡፡ ሰዎች የግል ጥቅማቸውን ካስቀደሙ ፍቅርን ይጥላሉ፡፡   
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ ፊልጵስዩስ 3፡8-9
ሰዎች ምድራዊ ነገር የሚማርካቸው ከሆነ መንፈሳዊውን ነገርን ይጥላሉ፡፡ ለምድራዊው ነገር ይበልጥ ዋጋ የሚሰጡ ሰዎች መንፈሳዊ ነገርን አይቀበሉትም፡፡ የመጣላችን ችግሩ እኛ ሳንሆን ሰዎች እኛን የሚጥሉበት መመዘኛ ሊሆን ይችላል፡፡
እላለሁ መጨረሻቸው ጥፋት ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው ክብራቸው በነውራቸው ነው ሃሳባቸው ምድራዊ ነው፡፡ ፊሊ 3፥18
በሰው መመዘኛ ሰውን የማይጥለው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ሰዎች አልተቀበሉንም ጣሉን ማለት እግዚአብሄር ጣለን ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መመዘኛ ከሰው መመዘኛ ይለያል፡፡ ሰዎች ያልተቀበሉትን እግዚአብሄር ሊቀበል ይችላል፡፡
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው። 1ኛ ሳሙኤል 16፡7
ሁልጊዜ የሚጥሉን ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የሚያከብሩን የሚቀበሉን ጥቅማችንን የሚረዱ ሰዎች አሉ፡፡
በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥1 ጴጥሮስ 24
ኢየሱስን የሚጥሉ ሰዎች እኛን ይጥሉናል፡፡ የኢየሱስን የመፅሃፍ ቅዱስ ትምህርት የሚጥሉ ሰዎች የእኛን ትምህርት ይጥላሉ፡፡
ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። ዮሃንስ 15፡18
ኢየሱስ የመጣልና የመናቅ ምሳሌያችን ነው፡፡ ኢየሱስ በዚያ ሁሉ ክብሩ በሰዎች ከተጣለ የእኛ መጣል ሊያስደንቀን አይገባም፡፡  
የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። ኢሳይያስ 533
የእግዚአብሄርን ልጅ ኢየሱስን ስንከተልና ፈቃዱን ስናደርግ እኛን የጣለ ሰው ችግሩ እኛ አይደለንም፡፡ እኛን የጣለ ሰው መጀመሪያ የጣለው ጌታን ነው፡፡
የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል። ሉቃስ 10፡16
ሰው በሰው መመዘኛ ተጣለ ማለት በእግዚአብሄር መመዘኛ ተጣለ ማለት አይደለም፡፡ ሰውእ እጀግ አስፈላጊውን የህይወታቸውን ክፍል በስህተት ይጥላሉ፡፡ ሰዎች በስህተት መድሃኒታቸውን ይጥላሉ፡፡ ሰዎች ስለጣሉት መድሃኒት መድሃኒትነቱን አያጣም፡፡
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ መዝሙር 118፡22
ሰው በአንዱ ሰው ተጣለ ማለት በሁሉም ሰው ይጣላል ማለት አይደለም፡፡ የእርሱን ዋጋ የሚረዳ ፣ የእርሱን አብሮነት የሚፈልግና የእርሱን ጥቅም የሚረዳ ሰው ደግሞ አለ፡፡ የተጣለ ሰው ለጣሉት ሰዎች ምህረትን በማድርግ የሚቀበሉት ሰዎች ላይ ማተኮር የመጣልን ህመም ይቀንስለታል፡፡
በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡8-9
የሞት ሽታ የምንሆንባቸው ሰዎች እንዳሉ የህይወት ሽታ የምንሆንባቸው ሰዎች ደግሞ አሉ፡፡
በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው? 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡15-16
ካለአግባብ አይጥለኝም ብለን የምንተማመንበት እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፥ ርስቱንም አይተውምና መዝሙር 94፡14
በእግዚአብሄር ዘንድ ትክክል መሆናችንን ማረጋገጥ እንጂ በሰው መፈረድ ወይም መጣል ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ የሰው ቁጣ የእግዚአብሄርን ፅድቅ አይሰራም፡፡ (ያዕቆብ 1:20)
ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ወይም በሌላ ሰው ዘንድ ብፈረድ ለእኔ ምንም አይደለም፤ እኔም በራሴ እንኳ አልፈርድም፤ በራሴ ላይ ምንም አላውቅምና፥ ነገር ግን በዚህ አልጸድቅም፤ እኔን የሚፈርድ ግን ጌታ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡1-3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መጣል #መሰደድ #መገፋት #መውደቅ #አለመመረጥ #ተቀባይነትማጣት #ዋጋአሰጣጥ #አእምሮ #ልብ #ኢየሱስ #ጌታ #መፅሃፍቅዱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አምልኮ #እምነት #ነፃነት #መስማት #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment