Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, June 20, 2018

መኖርን አይርሱ!

መጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ለመጨረስ እና ኮሌጅ ለመጀመር እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡
ከዚያ ደግሞ ኮሌጅን ለመጨረስ እና ሥራ ለመጀመር እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡
ከዚያም ለማግባት እና ልጆች ለመውለድ እስከሞት ድረስ እጓጓ  ነበር፡፡
ከዚያ በኋላ ወደ ሥራዬ መመለስ እንድችል ልጆቼን ለትምህርት የሚያበቃ ዕድሜዬ እንኪደርሱ እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡
ከዚያ በኋላ ጡረታ ለመውጣት እስከሞት ድረስ እጓጓ ነበር፡፡
እና አሁን ለመሞት ተቃርቤያለሁ . . .
በድንገት የተረዳሁት ነገር በህይወቴ ዘመን ሁሉ የሚቀጥለው ደረጃ ላይ ለመድረስ እጅግ ስጓጓ ነገር ግን መኖርን ረስቼ እንደነበር ነው፡፡ ይላል አንድ የእድሜ ባለጠጋ ሰው፡፡
ይህ የሁላችንም ፈተና ነው፡፡ ሁላችንም አንድ ደረጃ ላይ መድረስ ፣ አንድን ግኝት ማግኘት ፣ ስኬት ላይ መድረስና በያዝነው ነገር ድልን መቀዳጀት እንፈልጋለን፡፡
ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ በህይወት መትጋት መፅሃፍ ቅዱሳዊ መርሆ ነው፡፡
ነገር ግን መትጋት ብቻ ሳይሆን የተጋንበትን ነገር ማጣጣም እንዲሁ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው፡፡ ማግኘት ብቻ ሳይሆን ያገኘነውን ነገር ጊዜ ወስደን ማጣጣም መጠቀምና በዚያ መደሰት መፅሃፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ ነው፡፡
ማግኘት አንድ ነገር ነው ያገኘነውን መጠቀም ሌላ ነገር ነው፡፡ እንድናገኝ ብቻ ሳይሆን ያገኘነውን ነገር እንድንጠቀንም እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
አንዳንድ ሰው ገንዘብን ለማግኘት እጅግ ሲጥር ታዩታላችሁ፡፡ ጥረቱም ይሳካለታል ገንዘብን ያገኛል፡፡ በመሃል ግን ገንዘብን ለማግኘት የሰራበትንና የለፋበትን ምክኒያት ይረሳዋል፡፡ ገንዘቡን አይጠቀምበትም፡፡ ገንዘቡ ህይወቱን አያመቻችለትም፡፡ ገንዘቡ መሰረታዊ ፍላጎቱ አያሟላለትም፡፡ ገንዘቡን ያከማቸዋል፡፡ ገንዘቡን በማየት ብቻ ይረካል፡፡ ገንዘቡ የተጠራቀመበት ምክኒያት ይጠፋል፡፡ ገንዘቡ ጥቅም ላይ አይውልም፡፡ ገንዘቡ ባለገንዘቡን ሳይረዳው ይቀራል፡፡
የዚህ ሰው ችግሩ ገንዘብ መስራት ያውቃል ነገር ግን ገንዘቡን መጠቀም አልተማረም፡፡ ገንዘብ ለመስራት ሰልጥኗል ገንዘብን ለመጠቀም አልሰለጠነም፡፡ ገንዘቡን እንዴት እንደሚያገኘው እውቀት አለው ገንዘቡን እንዴት በሚገባ እንደሚጠቀምበት እውቀት ይጎድለዋልን፡፡
እግዚአብሄርን የማያውቁ ሰዎች በዚህ እጅግ ይቸገራሉ፡፡ ያገኙትን ገንዘብ ወይ ሳይጠቀሙበት አካብተውት አካብተውት ያልፋሉ፡፡ ደስታቸውን ሁልጊዜ ለወደፊት ያስተላለፉታል፡፡ ይህ ሲሆንልኝ መደሰት እጀመራለሁ ይላሉ፡፡ ልክ እንደደረሱበት ሲያውቁ አሁን ያሉበት ደረጃ በራሱ ግኝትና ስኬት እንደሆነ ይዘነጉታል፡፡ ዛሬ ያሉበትን ደረጃ ይንቁታል፡፡ በዛሬ ባሉበት ደረጃ መደሰት አያውቁም፡፡ ዛሬ ላይ ሲደርሱ ስለማያውቁት ስለነገ ይጓጓሉ፡፡ ዛሬ ላይ ሲደርሱ የዛሬን ድል እርግፍ አድርገው ትተው ሳይደሰቱበት ስለነገ ብቻ ማውራት መጨነቅ ማሰብ ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ ነው ህይወታችንን በቀን ከፋፋልን እንድንደሰትበት መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተንምረን፡፡
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡34
ህይወት በትጋት የምንወጣው ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን ቀስ ብለን የምንደሰትበት ስጦታ ነው፡፡
የእግዚአብሄ ስጦታ ሁለት ነው፡፡ እግዚአብሀር በህይወት አንዲከናወንልን ትጋትን ይሰጠናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሀነ የደረስብነትን ግኝት ረጋ ብለን እንድናጣጠምው እውቀትን ይሰጠናል፡፡
ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል።መጽሐፈ መክብብ 8፡15
እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ። ሁልጊዜ ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባትም ከራስህ ላይ አይታጣ። በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ። መጽሐፈ መክብብ 9፡7-9
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #መደሰት #ስኬት #ህይወት #ስጦታ #በረከት #ስኬት #ዛሬ #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ትጋት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #ነገ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #ማስተዳደር #እረፍት

No comments:

Post a Comment