Popular Posts

Saturday, June 2, 2018

ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ

በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ፊልጵስዩስ 2፡14-15
በምድር ላይ ያለነው ለአለም ብርሃን ለመሆን ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው ስለእግዚአብሄርን በጎነት ለመመስከር ነው፡፡
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9
ሰዎች የምናስበውን የምንናገረውንና የምናደርገውን ነገር በቅርበት ይከታተላሉ፡፡ በምንናገረውና በምናደርግው ነገር ለእግዚአብሄር መንግስት ጥሩ ወይም መጥፎ ምስክር ልንሆን እንችላለን፡፡ በምንናገረው ነገር ሰዎች ቤተክርስትያንን እንዲያምኑ ወይም እንዲጠራጠሩ ልናደርግ እንችላለን፡፡ በምንናገረው ነገር ሰዎች አገልጋዮችንና መሪዎችን እንዲሰሙ ወይም እንዳይሰሙ ማድረግ እንችላለን፡፡ በምንናገረው ነገር ሰዎች ወደ እግዚአብሄር መንግስት እንዲመጡ ወይም እንዳይመጡ ልናደርግ እንችላለን፡፡   
የሚያንጎራጉር ሰው ሰይጣን ስራ እንጂ ስለ እግዚአብሄር መልካምነት ሊመሰክር አይችልም፡፡ የሚንጎራጉር ሰው ስለሰይጣን ጨለማ እንጂ ስለእግዚአብሄር ብርሃን ምስክር ሊሆን አይችልም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ስለሰይጣን ሃይልነት እንጂ ስለእግዚአብሄር ሃያልነት አይናገርም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ስለሰይጣን ተንኮል እንጂ ስለሚበልጠው ስለእግዚአብሄር ጥበብ ሊመሰክር አይችልም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ስለሃጢያት ብርታት እንጂ ስለእግዚአብሄር ፀጋ ብርታት ሊመሰክር አይችልም፡፡
የሚያንጎራጉር ሰው ጥያቄ ያለበት እንጂ ጥያቄው የተመለሰለት ሰው አይደለም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ኢየሱስ ጥያቄን ይመልሳል ብሎ የሚመሰከር ህይወትም አንደበትም የለውም፡፡
የሚያንጎራጉር ሰው ሌላውን ሰው ወደ እግዚአብሄር መንግስት አያበረታታም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ሌላው ወደእግዚአብሄር መንግስት እንዳይመጣ እንቅፋት ይሆናል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው ሌላው እግዚአብሄርን እንዲያገለግል አያበረታታም፡፡ የሚያንጎራር ሰው ሌላው ለእግዚአብሄር እንዳይሰጥ ያዳክማል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የሰዎችን በጎ ህሊና ያበላሻል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የሰዎችን እምነት ይሰርቃል፡፡ የሚያምጎራጉስር ሰው የሰዎችን ልብ ያወርዳል፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የሰዎችን ተስፋ ያጨልማል፡፡  
የሚያንጎራጉር ሰው የተሸነፈ ሰው ነው፡፡ የተሸነፈን ሰው ለመከተል የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የአሸናፊነት መንገድ የጠፋበት ሰው ነው፡፡ የአሸናፊን መንግስት እንጂ ተሸናፊን መንግስት ውስጥ መግባት የሚፈልግ ሰው እንደሌለ ሁሉ የሚያንጎራጉር ሰው ለእግዚአብሄር መንግስት ምስክር መሆን አይችልም፡፡
የሚያንጎራጉር ሰው ምህረትን እንድናደርግና ቻይ እንድንሆንና ቸር እንድንሆን የሚያስተምረውን የኢየሱስን ትምህርት ይቃወማል፡፡
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ማቴዎስ 5፡39-41
የሚያንጎራጉር ሰው ስለራሱ ድካም እንጂ ስለሚሸንፈነው የእግዚአብሄር ፀጋ ሊመሰክር አይችልም፡፡ የሚያንጎራጉር ሰው የእግዚአብሄርን ፀጋ በሚያበዛለት በድካሙ የማይመካ ሰው ነው፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9
በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ፊልጵስዩስ 214-15
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #አታንጎራጉሩ #አታጉረምርሙ #ብርሃን #ምስክር #ጠማማ #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

No comments:

Post a Comment