Popular Posts

Monday, June 4, 2018

ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና

ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና
አገልግሎት የሚጀምረው ከግል ህይወት ነው፡፡ አገልግሎት የሚጀምረው ከራስ ነው፡፡ ሌሎችን የማገልገሉ መሰረት ራስን ማገልገል ነው፡፡ ራሱን ያልጠበቀ ሰው ሌላውን ሊጠብቅ አይችልም፡፡ ራሱን ያላዳነ ሰው ሌላውን ሊያድን አይችልም፡፡ ሌላውን ለማዳን የራሱን መዳን ቸል የሚል ሰው ራሱንም ሌላውንም ማዳን የማይችል ጥበብ የጎደለው ሰው ነው፡፡   
ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና። 1 ጢሞቴዎስ 416
አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ
መፅሃፍ ቅዱስ ሌላውን ለማዳን በትጋት ማገልገል እንዳለብን ያስተምራል፡፡ ነገር ግን ራሳችን በፈተናው የምንወድቅ ከሆነ ቅድሚያ መስጠት ያለብን የራሳችን ከፈተናው መዳን እንጂ ራሳችን በፈተና በመውደቅ ሌላውን ማዳን አይደለም፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። ገላትያ 61
ህይወታችንን ለመጠበቅ ሃላፊነት ያለብን እኛ ነን፡፡ የእኛን ህይወት ለመጠበቅ የመጀመሪያው ሃላፊነት ያለብን እኛው ነው፡፡ የእኛ ህይወት ለእኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ህይወት ነው፡፡
ሌሎችን የምናገለግለው የእኛን ህይወት በማገልገል ፋንታ አይደለም፡፡ ሌሎችን የምናገለግለው በዋናችን አይደለም፡፡ ሌሎችን የምናገለግለው ራሳችንን አገልግለን ነው፡፡ ሌሎችን የምናገለግለው አገልገሎት የራሳችንን ህይወት ከነካ መተው አለብን እንደገና ተመልሰን ለራሳችን አገልግሎት ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡
ራሳችንን ጠብቀን የምናገለግለው አገልግሎት ብቻ ነው ሌሎችን ሊጠቅም የሚችለው፡፡ ራሳችንን ጠብቀን የምናገለግለው አገለግሎት ብቻ ነው ዘላቂነት ያለው፡፡ ራሳችንን ሳንጠብቅ መንፈሳዊ ህይወታችንን አደጋ ላይ እየጣልን የምናገለግለው አገልግሎት ኪሳራ ነው፡፡
ልብሳቸውን እንኳ እየጠላችሁ በፍርሀት
ተጠራጣሪ ለሆኑት ራሩላቸው፤ አንዳንዶችን ከእሳት ነጥቃችሁ አድኗቸው፤ ለሌሎች ደግሞ በርኩስ ሥጋ የተበከለውን ልብሳቸውን እንኳ እየጠላችሁ በፍርሀት ምሕረት አሳዩአቸው። (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)ይሁዳ 1፡22-23
ቃሉን ስናነብ የምናነበው ለራሳችን ህይወት ነው፡፡ ቃሉን ስናነብ የምናነበው ለምናገለግለው ሰው አይደለም፡፡ ለራሳችን ያነበብነውና የኖርነው ቃል ብቻ ነው ሌሌውን ሊጠቅም የሚችለው፡፡
እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። ይሁዳ 1፡20-21
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራስ #ራስህን #ጠብቅ #ለራስህ #ተጠንቀቅ #ቃል #ህይወት #አገልግሎት #አምልኮ #ፀሎት #ጥሪ #ተመልክተን #መቃጠል #መቀጣጠል #ክብር #አገልግሎት #መዋረድ #መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment