Popular Posts

Friday, March 9, 2018

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ ዮሃንስ 2፡17
አሁን የምታዩት ነገር ሁሉ እንዲያልፍ ተወስኖበታል፡፡ ይህ የማያልፍ ለዘላለም የሚኖር የሚመስለው አለም ያልፋል፡፡ ይህ ብልጭልጩ ነገር ሁሉ አንድ ቀን ያልፋል፡፡ አለም የምንተማመንበት ዘለቄታዊ ነገር አይደለም፡፡ አለም ተስፋ የምናደርገው ቋሚ ነገር አይደለም፡፡
ሰማይና ምደር ስለሚያልፉ የእግዚአብሄር ቃልና የእግዚአብሄርን ቃል የሚያደርጉ ብቻ አያልፉም፡፡
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። ማቴዎስ 24፡35
ሰማይና ምድር ያልፋሉ የእግዚአብሄር ቃልና በእግዚአብሄር ቃል የተሰሩ ነገሮች አያልፉም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ያለተሰሩ ነገሮች ሁሉ ሊለፋባቸው የሚገቡ ቋሚ ነገሮች አይደሉም፡፡
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። ዮሃንስ 6፡27
አለምና ምኞቱ ያልፋሉ የእግዚአብሄር ቃልና የማይታየው ነገር ሁሉ አያልፍም፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
አለምና ምኞቱ ያልፋሉ በእግዚአብሄር ፈቃድ የተደረገ ነገር ብቻ አያልፍም፡፡
በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል። 2ኛ ጴጥሮስ 3፡10
አለምና ምኞቱ ያልፋሉ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት የተገነቡ ስራዎች ብቻ ይፀናሉ፡
ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡11-15
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ፈቃድ #ተስፋ #ፍፃሜ #አለም #ምኞት #እሳት #ጊዜያዊ #ዘላለማዊ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተሰፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment