ንጉሥሽ
ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ! ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መክብብ 10፡16-17
በመሰረታዊ
ፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ በህይወት ስኬታማ እንድንሆን ከሚያደርጉ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ጥበቦች ውስጥ አንዱ
ነው፡፡
በመሰረታዊ
ፍላጎትና በቅንጦት መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ የሃብታምም የደሃም ሃላፊነት ነው፡፡ ሃብታምም ለመሰረታዊ ፍላጎት የተሰጠውን ስጦታ
በቅንጦት ላይ አባክኖ ይቸገራል፡፡ ደሃም ለመሰረታዊ ፍላጎት የተሰጠውን ስጦታ በቅንጦት ላይ አባክኖ ይቸገራል፡፡ ቅንጦት የገንዘብ
ጉዳይ ሳይሆ የአእምሮ ጉዳይ ነው፡፡
መፅሃፍ
ቅዱስ ንጉስ እንኳን በመሰረታዊ ፍላጎትና በቅንጦት መካከል መለየት ካልቻለ እንደማይሳካለት ያስተምረናል፡፡ በመሰረታዊ ፍላትና በቅንጦት
መካከል መለየት የማይችል ሰው የተማረ ሊሆን ይችላል ፣ ዝነኛ ሊሆን ይችላል ፣ ባለስልጣን ሊሆን ይችላል ፣ ባለጠጋ ሊሆን ይችላል
አይሳካለትም፡፡ በመሰረታዊ ፍላትና በቅንጦት መካከል መለየት የማይችል ሰው ንጉስ ቢሆን እንኳን ህዝቡንና ሀገሩን የሚከተሉትን ሰዎች
ይዞ ይጠፋል፡፡
ሰው
በቃኝ ማለትን ካልተማረ ለምንም አይጠቅምም፡፡ ሰው ያለኝ ይበቃኛልን ካላወቀ ህይወቱን በሙሉ ሲበላላና የምግብ ፍላቱን ሲያሟላ ማንንም
ሳይጠቅም ማንንም ሳያገለግል የተፈጠረበትን አላ ስቶ ህይወቱን ያባክናል፡፡
የሰው
ንግስናው በቃኝ ማለቱ ነው፡፡ የሰው ክብሩ ያለኝ ይበቃኛል ማለቱና ባለው መርካቱ ነው፡፡ የሰው ክብሩ ከራሱ አልፎ ለሌላው ማሰቡ
ነው፡፡ የሰው ክብሩ ከራስ ወዳድነት ወጥቶ ሰውን መውደዱና ማገልገሉ ነው፡፡
አንድ
ሰው ሲናገር ሃብታም ማለት ለመኖር ብዙ የማያስፈልገው ሰው በማለት ራስን ማማጠንና በቃኝ ማለት ሃብት እንደሆነ ተናገረ፡፡
ስለዚህ
ነው ራሱን የሚያማጥን ሰው ደሃ ሊሆን አይችልም ፣ ራሱን የማያማጥን ሰው ሃብታም ሊሆን አይችልም የሚባለው፡፡
የሰው
ውድቀቱ በቃኝ አለማለቱ ነው፡፡ የሰው ውድቀቱ ራሱን አለማማጠኑ ነው፡፡ የሰው ውድቀቱ የሚፈልገውንና የሚያስፈልገውን ለይቶ አለማወቁ
ነው፡፡ የሰው ውድቀቱ ከራሱ አልፎ ለሌላ አለማሰቡ ነው፡፡
ንጉሥሽ
ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ! ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር
ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መክብብ 10፡16-17
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #መሰረታዊፍላጎት #ቅንጦት
#ማማጠን #ህፃን #ንጉስ #መኳንንት #ፀሎት #ልመና
#ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment