ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር አላማ ነው፡፡ ሰው
ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረለት አላማ ነበር፡፡ ሰው እንዲፈጠር ያደረገው የሚፈፅመው አላማ ስለነበረ ነው፡፡
በሰው አእምሮ ውስጥ ብዙ ሃሳብ አለ፡፡ ሰው አንዱን
ሲያገኝ ሌላ ያስባል፡፡ ሰው አንዱን ሲደርስበት ሌላ ያቅዳል፡፡ የሰው ሃሳብና እቅድ አያልቅም፡፡ የሰው ሃሳብና እቅድ ከራስ ወዳድነት
ላይፀዳ ይችላል፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር
አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
የእግዚአብሄር አላማ ከሰው አቅድ ይበረታል፡፡
የእግዚአብሄር አላማ ከሰው አሰራር ይበረታል፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ከሰው ፍላጎት ያይላል፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳ 19፡21
የእግዚአብሄር
ሃሳብ አይከለከልም፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ ሊያስቆም የሚችል ሃይል የለም፡፡ እግዚአብሄር ካሰበ ይሆናል፡፡
ሁሉን
ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ኢዮብ 42፡2
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ራእይ #እይታ #አላማ #ተስፋ #ፍፃሜ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተሰፋ #ፍፃሜ #የእግዚአብሄርሃሳብ #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment