Popular Posts

Thursday, March 29, 2018

ስልጣን ወይስ ባህሪ?

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በባህሪው እንዲኖር ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረው ሰው የእግዚአብሄር ባህሪዎች ሁሉ ነበሩት፡፡
እግዚአብሄር የፈጠረው እግዚአብሄር አታድርግ የተባለውን ያንኑ ነገር በማድረጉ የተነሳ ከእግዚአብሄር ክብር ወደቀ፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ከመታዘዘ ይልቅ ተጨማሪ ሃይል ሲፈልግ የእግዚአብሄርን ባህሪ አጣው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ላይ በማመፁ እነዚያን የእግዚአብሄር ባህሪያት እንዲሁም የፈለገውን ሃይል አጣው፡፡ ሰው እንደ እግዚአብሄር ለመሆን ባለው ጥማት የእግዚአብሄርን ባህሪ አጣው፡፡  
ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ዘፍጥረት 3፡5
አሁንም የሰው ስጋዊ ባህሪ መልካሙን የእግዚአብሄርን ባህሪ አይፈልግም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሃይልን ነው፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ጊዜን መቆጣጠር እንጂ ትእግስትን አይደለም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሰውን መቆጣጠር እንጂ ለሌላው መገዛትን አይደለም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሁኔታን መቆጣጠር እንጂ ራስን መስጠት አይደለም፡፡
የሰው ስጋዊ ባህሪ የሚፈልገው ሃይሉን በትክክል የሚያስተዳድርበትን የእግዚአብሄርን ባህሪ ሳይሆን ሃይሉን ብቻ ነው፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ ለሃይል ይጓጓል፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ አንደኛ መሆንን እንጂ ማገልገልን አይፈልግም፡፡ የሰው ስጋዊ ባህሪ መጠቀምን እንጂ መጥቀምን አያስበውም፡፡ ስጋ ለሃይል እንጂ ለባህሪ ግድ የለውም፡፡
የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው፦ መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት። እርሱም፦ ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን አሉት። ማርቆስ 10፡35-37
ስጋ በነገሮች መያዝ አይፈልግም፡፡ ስጋ መታገስ አይፈልግም፡፣ስጋ መጠበቅ አይፈልግም፡፡ ስጋ ሌላወን መውደድ አይፈልም፡፡ ስጋ ሌላውን መሸከም አይፈልግም፡፡ ስጋ የሚፈልገው ሌላውን ሁሉ መለወጥን እንጂ መታገስን አይደለም፡፡ ስጋ የሚፈልገው ሌላውን መተው እንጂ መውደድ አይደለም፡፡
ስጋ መናገርን እንጂ መስማትን አይፈልግም፡፡ ስጋ በንግግር ሁሉንም መቆጣጠርን እንጂ መስማትን አይፈልግም፡፡  
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው። ያዕቆብ 3፡2
ስጋ የሚፈልገው ነገሮችን መቆጣጠር እንጂ ራሱን መስጠት አይደለም፡፡ ስጋ የሚፈልገው ሌላውን ሰው እንደርሱ ማድረግን እንጂ ሌላውን ሰው መምሰልን አይደለም፡፡ ስጋ ሌላውን ሁሉ ዝቅ አድርጎ መግዛት እንጂ ማንሳት ማስታጠቅ መልቀቅ አይፈልግም፡፡
ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። ማቴዎስ 10፡39
ስጋ ተጨማሪ ሃይልን እንጂ የባህሪ ለውጥን አይፈልግም፡፡ ስጋ ተጨማሪ ስልጣንን እንጂ መገዛትን አይፈልግም፡፡
በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡1-3
ስለዚህ ነው ሃዋሪያው ጳውሎስ ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ የሚለው፡፡
ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡27
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ስጋ #ምኞት #ማሰብ #ህይወት #ሞት #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና

No comments:

Post a Comment