የጐመን
ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። ምሳሌ 15፡17
ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው
የተፈጠረው ለሰላም ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለፍቅር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በሰላም እብሮ እንዲኖር ነው፡፡ ስው የተፈጠረው በፍቅር
ተጋግዞ እንዶኖር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በሰላም ተረዳደቶ እንዶኖር ነው፡፡
ሰው ለጥል አልተፈጠረምን፡፡ ሰው ለረብሻ አልተፈጠረም፡፡
ሰው ለመነካከስ አልተፈጠረም፡፡
ስለዚህ ነው ሰው ሁሌ ሰላምን ከረብሻ የሚመርጠው፡፡
ስለዚህ ነው ሰው ሁሌ ፍቅርን ከጥላቻ የሚመርጠው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ሁሌ
ፍቅር የሌለው ሰው ሃብት ቢኖረው ምንም አይጠቅመውም፡፡
ሰላም የሌለው ሰው ሃያል ቢሆን ምንም አይጠቅመውም፡፡ እረፍት የሌለው ሰው ጥበብ ቢኖረው ምንም አይጠቅመውም፡፡
ስለዚህ ነው ሰው ከረብሻ ከሃብታምነት ይልቅ ሰላምን
የሚመርጠው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ውዝግብ ዝና ይልቅ እረፍትን የሚመርጠው፡፡ ስለዚህ ነው ሰው ከእረፍት የለሽ ጥበብ ይልቅ እርካታን
የሚመርጠው፡፡
የእግዚአብሄር
በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች ሃዘንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም፡፡
የእግዚአብሔር
በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርስዋ ጋር አይጨምርም። ምሳሌ 10፡22
እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል። የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። ምሳሌ 15፡16-17
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል
#ፍቅር #ጥል #በረከት #ጎመን #ፍሪዳ #ሰላም #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን
#የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #እረፍት
No comments:
Post a Comment