ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬያለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች። መዝሙር 139፡14
እግዚአብሔር
የፈጠረን ለክብሩ ነው፡፡
ለክብሩ
ሲፈጠርን ግሩምና ድንቅ አድርጎ ነው፡፡
እገዚአብሄር
የፈጠረን ለአላማው ነው፡፡ እግዚአብሄር ሲፈጠረን ለአላማው የሚያስፈለገውን ነገር ሁሉ በእኛ ውስጥ አድርጎ ነው፡፡ ለአላማው የሚያስፈልግው
ነገር ሁሉ በእኛ ውስጥ አለ፡፡
ቁመታችን
፣ የቆዳ ፣ ቀለማችን ፣ ዘራችን ፣ ባህሪያችን ፣ አስተዳደጋችን ሁሉ ለአላማው እንዳያንስም እንዳይበዛም ምጥን ተደርጎ ነው የተፈጠረው፡፡
እግዚአብሄር
ለጠራን ለአላማው ምንም አይጎድልብንም፡፡
እያንዳንዳችንን
ለልዩ አላማ ፈጥሮናል፡፡
የእኛ
የህይወት ስጦታዎች ሁሉ ለህይወት አላማችን በቂ ናቸው፡፡ የጎረቤታችን የህይወት ስጦታ ሁሉ ለጎረቤታችን የህይወት አላማ በቂ ነው፡፡
የእኛ
የህይወት አላማ ከጎረቤታችን የህይወት አላማ ጋር አይገናኝም፡፡ የእኛ ስጦታ ከጎረቤታችን ስጦታ ጋር አይገናኝም፡፡
ስለዚህ
ነው የባልንጀራህን ቤት አትመኝ የሚለው፡፡ ባልንጀራህ ከአንተ የተለየ ምንም የሚያስመኝ ነገር የለውም፡፡
የባልንጀራህን
ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ። ዘጸአት
20፡17
አፈጣጠርህ
ላይ ጉድለት እንዳለብህ የሚነግርህን ማንንም ሰው አትስማ፡፡ ምን አላማ በህወትህ እንዳለ የሚያውቅ ምን እንደሰጠህ የሚያውቅ እግዚአብሄር
ብቻ ነው ስላንተ ሊናገር የሚችለው፡፡
ግሩምና
ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬያለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች። መዝሙር 139፡14
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ግሩም #ድንቅ #በክርስቶስ #መንፈስ #ማንነት #መልክ #አምሳል #የእግዚአብሄርልጅ #ክብር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ማየት #የእግዚአብሄርመንግስት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ #ማእረግ #ስልጣን #ከፍታ
No comments:
Post a Comment