አንተ
ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት፤ መብልዋን
በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች። ምሳሌ 6፡6-8
ውጤት
ለማግኘት ተግቶ መስራት አማራጭ የለውም፡፡ ተግተን ካልሰራን የሚሆን ምንም ነገር አይኖርም፡፡
ተግቶ
ለመስራተ ደግሞ የራስ አነሳሽነት ይጠይቃል፡፡
ከአልጋችን
የሚያስነሳን መጥሪያ ሰአት መሆን የለበትም፡፡ ከአልጋችን የሚያስነሳን በውስጣችን ያለው የህይወት አላማ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ከአልጋችን
የሚያስነሳን የአገልግሎት ሸክም መሆን አለበት፡፡ ከአልጋ የሚያስነሳን የአገልግሎት ጥሪ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ተግተን እንድንሰራ
የሚያደርገን የሰዎች ማስታወስ ጉትጎታ መሆን የለበትም፡፡ የምንሰራው በራሳችን አነሳሽነት መሆን አለበት፡፡
ሁል
ጊዜ ሰው እንዲያስታውሰው እንዲጎተጉተው እንዲያነሳሳው የሚፈልግ ሰው ትጉህ ሰው አይደለም፡፡ ካላስታወሱት የማያስታውስ ካልጎተጎቱት
የማይሰራ ካላነሳሱት የማይነሳሳ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት ዘበት ነው፡፡
ገብረ
ጉንዳን መሪ የማይፈልግ ራሱን የሚያነሳሳ ሌላ እንዲጎተጉተው የማይፈልግ ትጉህ ሰው ምሳሌ ነው፡፡
ገበር
ጉንዳን ለሌላው አይደለም የሚሰራው፡፡ ገብረ ጉንዳን የሚሰራው ለራሱ ነው፡፡ ገብረ ጉንዳን የሚጎተጉተው አይፈልግም፡፡ ገብረ ጉንዳን
ራሱ የተነሳሳ ስለሆነ የሚያነሳሳው አይፈልግም፡፡
ገብረ
ጉንዳን የምትነሳሳው አዛዥ አነሳስቷት አይደለም፡፡ ገብረ ጉንፈን የምትተጋው አለቃ ፈርታ አይደለም፡፡ ገብረጉንዳን የምትሰራው ለራስዋ
ስትል ነው፡፡ ገብረ ጉንዳን የምትሰራው ውስጧን ስለሚጎተጉታት ነው፡፡ ገብረጉንዳን በትጋት የምትሰራው ለራሷ እርካታ ነው፡፡ ተገፍቶ
፣ ተባብሎ ፣ ተለምኖና ተጎትጉቶ የማይሰራ ሰው የተባረከ ነው፡፡
እንደ
ገብረ ጉንዳን ያለ ትጉህ ሰራተኛ ያገኘ ቤተሰብ ፣ ህብረተሰብ ፣ ቤተክርስተያንና ሃገር የተባረከ ነው፡፡
አንተ
ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት፤ መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች፥
መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች። ምሳሌ 6፡6-8
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ትጋት #ስራ #መድከም #ጕንዳን #ሸክም #ጥሪ #አላማ #ግብ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #ትህትና #ልብ #እምነት
No comments:
Post a Comment