Popular Posts

Friday, March 2, 2018

የሚያዝኑ ብፁዓን

የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። ማቴዎስ 5፡4
እግዚአብሄር በጌታ ደስ እንዲለን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ግን በጌታ ብቻ ደስ እንዲለን እንጂ በነገሮች ደስ እንዲለን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ እንድንመካ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ እንጂ በሌላ በምንም ነገር እንዳንመካ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በነገሮች ደስ እንዲለን ወይም እንድንኩራራ አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ እንጂ በነገሮች እንድንመካ አይፈልግም፡፡ በእርሱ እንጂ በነገሮች ከፍ ከፍ እንድንልን እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። 1ኛ ዜና 16፡10-11
እግዚአብሄር የሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ አንዲኖሩን ይፈልጋል ለዚያም በትጋት ይሰራል፡፡ እግዚአብሄር በሚያስፈልጉን ነገሮች ደስ እንድንሰኝ ግን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የሚያስፈልገንን ነገር በሚያሟላው በእርሱ ብቻ ደስ እንዲለን ይፈልጋል፡፡ በነገሮች የሚመካ ሰው በእግዚአብሄር ሊመካ አይችልም፡፡ በነገሮች ደስ የሚሰኝ ሰው በእግዚአብሄር ደስ ሊሰኝ አይችልም፡፡
በነገሮች የማይመካና ደስ የማይሰኝ ሰው በእግዚአብሄር ይመካል ደስ ይሰኛል፡፡ በነገሮች የሚያዝን ሰው በእግዚአብሄር ደስ ይለዋል፡፡እውነተኛ የቤተሰብነት የፍቅር ስሜት ካለን እኛ ቢሳካልን እንኳን የሌሎች አለመሳካት ያሳዝነናል፡፡ እኛ ብንድን አንኳን ሌሎች እስኪድኑ ድረስ ደስታችን ሙሉ አይሆንም፡፡
ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው። ማቴዎስ 9፡36
ፍቅር ሲኖረን በሚወድቁ ሰዎች እናዝናልን እንጂ አንደሰትም፡፡ ከቅናት ነፃ ስንወጣ የሚያሳዝነን እንጂ የሚያስደስተን የማንም ሰው ውድቀት አይኖርም፡፡
ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡7-8
እግዚአብሄርን ስንወድ እግዚአብሄርን የሚያስደስቱት ነገሮች ያስደስቱናል እግዚአብሄርን የሚያሳዝኑት ነገሮች ደግሞ ያሳዝኑናል፡፡
ለሰዎች ርህራሄና ምህረት ካለን እናዝናለን፡፡ ሃዘን የርህራሄና የፍቅር ምልክት ነው፡፡ ፍቅርና ርህራሄ የሌለው ሰው ለሰው አያዝንም፡፡
እግዚአብሄር የሚመራን በሃዘን ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን እንድናገለግል ሲልከን ሰዎቹ ላሉበት ሁኔታ ሃዘን ይሰማናል፡፡ ሃዘን ወደ መፀለይና ወደ ማገልገል ይመራናል፡፡
ስለራሳችን ውድቀት ካላዘንን እውነተኛ መፍትሄ አይመጣም፡፡
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡10
ወጥቶም ብዙ ሕዝብ አየና አዘነላቸው ድውዮቻቸውንም ፈወሰ። ማቴዎስ 14፡1
ሃዘን ሁሉ ስህተት አይደለም፡፡ ሃዘን ያለንበትን ሁኔታ መረዳት ነው፡፡ ሃዘን ከነባራዊ ሁኔታ ጋር መገናኘት ነው፡፡ ሁልጊዜ በሁሉም ነገር ደስ እንዲለው የሚፈልግ ሰው ከእውነታ ጋር መገናኘት የማይፈልግ ሰው ነው፡፡ ሁልጊዜ በነገሮች መደሰት የሚፈልግ ሰው ከነባራዊ ሁኔታ መሸሽ የሚፈልግ ሰው ነው፡፡ ሁልጊዜ ደስ እንዲለው የሚፈልግ ሰው ከነባራዊ ሁኔታ ጋር መጋፈጥ የማይፈልግ ሰው ነው፡፡ ሁልጊዜ በነገሮች ደስ እንዲለው የሚፈልግ ሰው በሰው ሰራሽ አለም ውስጥ መደበቅ የሚፈልግ ፈሪ ሰው ነው፡፡
የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። ማቴዎስ 5፡4
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ድህነት #ብፅእና #በረከት #ቃል #ፀሎት #ሃዘን #ርህራሄ #የሚያዝኑ #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment