እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27
እግዚአብሄር ኢየሱስን ለምንከተል ሁላችን መንፈሱን ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሄር መንፈሱን የሰጠን ሁል ጊዜ እንዲመራን ነው፡፡ እግዚአብሄር መንፈሱ የሰጠን ስለ ሁሉም እንዲመራን ነው፡፡ እግዚአብሄር መንፈሱ የሰጠን በሰዎች አስተያየት ግራ እንዳንጋባ ነው፡፡ እግዚአብሄር መንፈሱን የሰጠን በሁሉም ነገር የሚመራን ነገር ስላለ ነው፡፡ እግዚአብሄ መንፈሱን የሰጠን በራሳችን ሃሳብ እነማ ማስተዋል እንኳን እንዳንደገፍ ነው፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ ምሳሌ 3፡5
አንዳንድ ጊዜ የቤተክርስተያነ መሪዎች ተከታዮቻቸውን በእያንዳንዱ የህይወት ክፍላቸው ለመምራት ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜም መሪዎች እግዚአብሄር ለህዝቡ ያልሰጣቸውን ሸክም ተከታዮቻቸው ላይ ይጭናሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቤተክርስትያን መሪዎች ህዝቡ በእግዚአብሄር መንፈስ እንዲመራ እድል አይሰጡትም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቤተክርስትያነ መሪዎች ህዝቡ መንፈሱን እንዲከተል ነፃ አያደርጉትም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቤተክርስትያን መሪዎች ይህ ሃጢያት ነው ይህ ሃጢያት አይደለም በማለት የእግዚአብሄርን ህዝብ በእያንዳንዱ ነገር ይመራሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ አማኞች ራሳቸው እግዚአብሄር ያልሰጣቸውን ይሸከማሉ፡፡ አንዳድ ጊዜ እግዚአብሄር ያልሰጣቸውን ለማድረግ ሲሞክሩ ይወድቃሉ በዚያም ያማርራሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክርስትያኖች እግዚአብሄር ያልተናገራቸውን ነገር ተናግረው ራሳቸውን ይኮንናሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክርስትያኖች እግዚአብሄር ባልወቀሳቸው ነገር ራሳቸውን በመውቀስ ራሳቸውን ያጎሳቁላ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ክርስትያኖች ሌሎች ሰዎች ያሉዋቸውን ሰምተው ራሳቸውን ይኮንናሉ፡፡ ክርስትያኖች ከሰው አስተያየት ብቻ ተነስተው እግዚአብሄር ያልወቀሳቸውን ወቀሳ በላያቸውን ላይ ያመጣሉ፡፡
ሃዋሪያው ጳውሎስ ስለሚፈርዱበት ሰዎች እንዲህ ይላል፡፡
ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ወይም በሌላ ሰው ዘንድ ብፈረድ ለእኔ ምንም አይደለም፤ እኔም በራሴ እንኳ አልፈርድም፤ በራሴ ላይ ምንም አላውቅምና፥ ነገር ግን በዚህ አልጸድቅም፤ እኔን የሚፈርድ ግን ጌታ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 4፡3-4
ሃዋሪያው ጳውሎስ ከሰው ፍርድ ተነስቶ ራሱ ላይ አይፈርድም ራሱን አይኰንንም ፡፡
ሃዋሪያው ጳውሎስ ከራሱንም አስተሳሰብ እንኳን ተነስቶ ራሱን እይኲንንም፡፡
ሃዋሪያው ጳውሎስ የሚቀበለው አንድ ፍርድ በውስጡ የሚሰማውን የመንፈስን ቅዱስን ድምፅ ብቻ ነው፡፡ የሰውን ድምፅ የሚሰማው በውስጡ ካለው ከመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ጋር ከተስማማ ብቻ ነው፡፡ የራሱንም ሃሳብ የሚቀበልው እውነት እንደሆነ በውስጡ ያለው መንፈስ ቅዱስ ከመሰከረለት ብቻ ነው፡፡ ካለበለዚያ ግን ሰው የሚፈርድበትንም ሆነ ራሱ በራሱ ላይ የሚፈርደውን ፍርድ አይቀበልም፡፡
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment