Popular Posts

Tuesday, March 20, 2018

በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ

ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ ፊልጵስዩስ 3፡13
የኋላ ታሪክ ያለፈ ታሪክ ነው፡፡ መልካም ይሁን አይሁን ስለኋላችን አሁን ማድረግ የምንችለው ምንም ነገር የለም፡፡
እኛው ራሳችን ኋላችንን መልሰን ካላመጣነው አሁን በህይወታችን ላይ የሚፈጥረው ምንም ተፅእኖ የለም፡፡ ምንም ብናስበውና ብናሰላስለው ብንመፅም ትናንትን መለወጥ አንችልም፡፡ ትናንት አልፎዋል፡፡ ያለን ቀን ዛሬ ብቻ ነው፡፡  
የኋላችንን ስኬት መልሰን ካመጣነውና በዚያ ላይ ከቆየንና ከተኩራራን ግን በወደፊት ህይወታችን ላይ የሚያመጣው ትልቅ ጉዳት አለ፡፡ በኋላችን ታሪክ ላይ ብዙ ከቆየን የወደፊት ህይወታችንን ያዘገየዋል ብለም ያጨናግፈዋል፡፡ በኋላችን ታሪክ ላይ ብዙ ከቆየን ወደፊት መራመድ ሲገባን የኋላ ኑሮዋችንን ደግምን ስለምንኖረው አሁናችንን እናበላሸዋለን፡፡
አሁን አዲስ ቀን ነው፡፡ አሁን አዲስ እድል ነው፡፡
ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ሰቆቃው ኤርምያስ 3፡22
በኋላችንን ስኬት ላይ ብቻ ሳይሆን በየኋላችን ውድቀት ላይ ብዙ ከቆየንና ከተቆጨን ሳናውቀው የኋላችንን ህይወት እንደገና እንኖረዋለን፡፡ በዛሬ ላይ ትናንተን ከኖርነው ነገር እናበላሸዋለን፡፡ ነገርን ውጤታማ ለማድረግ ትናንተን ለትምህርትነት ብቻ እንጂ መተውና መርሳት ይጠይቃል፡፡
የእግዚአብሄር ሴት ጆይስ ማይር ስትናገር የኋላችሁን በጣም የምታስቡና የምታሰላስሉ ከሆነ የኋላ ህይወቴ ከወደፊት ህይወቴ ይሻላል እያላችሁ ነው፡፡ የኋላ ህይወታችሁ ግን ከወደፊት ህይወታችሁ በፍፁም አይሻልም፡፡ እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ እግዚአብሄር አያልቅበትም፡፡ እግዚአብሄር ለእናንተ ያዘጋጀው አዲስ ነገር አለ፡፡
በኋላ ስኬትም ይሁን ውድቀት ሳይያዙ ወደፊት መሄድ ጉልበት ይጠይቃል፡፡ በኋላ ስኬትም ይሁን ውድቀት ውስጥ ብዙ ሳይቆዩ ወደፊት መቀጠል ጥበብ ይጠይቃል፡፡ የኋላውን ውድቀትም ይሁን ስኬት እየረሱ ወደፊት መዘርጋት ወደ ውጤት ያደርሳል፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ ፊልጵስዩስ 3፡13
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጊዜ #ዘመን #ውብ #ዛሬ #ነገ #ትናንተ #ፀጋ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #ዛሬ #ነገ #ትላንት #መሪ 

No comments:

Post a Comment