ኃጢአተኞችን
ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15
የሰው
መንገድ በምርጫ የተሞላ ነው፡፡ ዛሬ የምንኖረው ኑሮ ትላንት የመረጥነውን ምርጫ ውጤት ነው፡፡ ወደፊት የምንኖረው ኑሮ ዛሬ የመረጥነውን
ምርጫ ውጤትን ነው፡፡
ሰው
በህይወቱ ዘመን ሁሉ በምድር ላይ ብዙ ምርጫ መምረጥ ቢጠበቅበትም እንደዚህ ያለ የወደፊት ህይወቱን ሁሉ የሚወስን ምርጫ ግን የለም፡፡
አንዳንድ
ምርጫ በገንዘባችን ላይ ተፅእኖ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሌላው ምርጫ በዝናችን ላይ ታላቅ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ ሌላው ደግሞ በጥበባችን
ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊን ተጽፅእኖን ያመጣል፡፡ ሌላውም በሃይላችን ላይ ተፅእኖ በማሳደር በምድር ላይ ሃያል እንድንሆን ወይም
እንዳንሆን ያደርገናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ምርጫዎች ተፅእኖ የሚያደርጉት የምድር ህይወታችንን ብቻ ነው፡፡
ነገር
ግን በምድርም ከምድር ህይወት በስቲያም ህይወታችን ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ወሳኝ ምርጫ አለ፡፡ ሰው በምድር ላይ ሲኖር በሌላ ምርጫዎች
እንኳን ቢሳሳት በዚህ ምርጫ ግን መሳሳት የለበትም፡፡ ሰው በምድር ላይ ሲኖር በሌላ ምርጫዎች የሚሳተው መሳሳት በዚህ መርጫ እንደሚሳሳተው
መሳሳት አይከፋም፡፡ ሰው በሌላ ምርጫ ቢሳሳት ውጤቱ የምድር እጦት ብቻ ነው፡፡ ሰው በምድር ምርጫዎች ቢሳሳት የምርጫው ውጤት በምድር
ላይ ብቻ ነው የሚቀረው፡፡
ሰው
ግን በዚህ መርጫ ቢሳሳት ውጤቱ የምድርን ቢያጠቃልልም የምርጫው ውጤት በምድር ላይ ብቻ አያበቃም፡፡ ሰው በዚህ ምርጫ ቢሳሳት ውጤቱ
በምድርና ከምድር ህይወት በኋላም ይቀጥላል፡፡ ሰው በዚህ መርጫ ቢሳሳት ውጤቱ የማይቀለበስ የዘላለም ነው፡፡ ሰው በዚህ መርጫ ቢሳት
ውጤቱ ለዘላለም ከእግዚአብሄር መለያየትን ያመጣል፡፡
ኃጢአተኞችን
ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት
#ወንጌል #ስብከት #ቃል #የታመነ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #ኢየሱስ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment