Popular Posts

Monday, March 19, 2018

ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው

ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ ሉቃስ 18፡1
በፀሎት ውስጥ የታመቀውን ታላቅ እድል የሚረዳው ኢየሱስ በምድር ህይወቱ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሁሉ ሰዎች እንዲፀልዩ አበረታቷል፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7፡7-11
ፀሎት ያታክታል፡፡ ፀሎት ለልፍስፍሶች አይደለም፡፡ ፀሎት ለግፈኞች ነው፡፡ ፀሎት እስኪያገኙ ለሚያንኳኩ ነው፡፡
ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ሉቃስ 18፡1፣7-8
ጸሎት ፀልዮ እጅግ ብዙ ነገሮችን የተቀበለው ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ ሁሉ ስለ ፀሎት በስፋት አስተምሯል፡፡
ሳያቋርጥ በመፀለይ በእግዚአብሄር በረከት ይኖር የነበረው ኢየሱስ ሳያቋርጡ እንዲፀልዩ በምሳሌ ጭምር ያስተምር ነበር፡፡
ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች፦ ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፦ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለ፦ ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? ሉቃስ 18፡1-8
ኢየሱስ ደጋግሞ ደጋግሞ እንዲፀልዩ የሚያበረታታበት ምክኒያቱ ሰዎች ታክተው ፀሎትን ካቆሙ ከእግዚአብሄር የሚያገኙትን ታላቅ በረከት ስለሚያጡ ነው፡፡ ሰዎች ደግሞ መታከትንና ድካም አሸንፈው ከፀለዩ በፀሎት የማይገቡበት በረከት ስለማይኖር ኢየሱስ ደጋግሞ ደጋግሞ እንዲፀልዩ ያበረታታ ነበር፡፡  
የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16
ሰዎች በእግዚአብሄር ሙሉ ባለጠግነት በረከት እንዲኖሩ የሚፈልግና ሰዎች የእግዚአብሄር በረከት እንዳይቋረጥባቸው የሚፈልግ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሳያቋርጡ እንዲፀልዩ አስተምሯዋል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ቃል #ፀሎት #ልመና #ሳይታክቱ #ዘወትር #እምነት #ሳታቋርጡ #እልፍኝ #እግዚአብሔር #መኖር #እምነት #መስማት #መታዘዝ #በቃሉመኖር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment