ስለኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እምነት ሲነሳ ስለቅዱሳንና
መላእክት ስግደት ፣ ስለማርያም አማላጅነት ስለመሳሰሉት ይነሳል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ዋና ነገር አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የምናምናቸው
መፅሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ነገሮች በክርስትና ህይወታችን ላይ ትልቅ ተፅእኖ ቢኖራቸውም ሰውን ክርስትያን የሚያደርገው በቅዱሳን ሰማእታት
አማላጅነት ማመኑ ወይም አለማመኑ አይደለም፡፡ ሰውን ክርስትያን የሚያደርገው ወይም የማያደርግው ለቅዱሳን እና ለሰማእታት የሚያደርገው
ስግደት የአምልኮ ወይም የአክብሮት ስግደት መሆኑና አለመሆኑ አይደለም፡፡
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር። ማቴዎስ 23፡23
አንዳንድ
ጊዜ የምንጣላው ዋና ባለሆኑ ነገሮች ላይ ነው፡፡ ዋናው ነገር ኢየሱስን መቀበላችን ነው፡፡ ዋናው ነገር ኢየሱስን በመቀበላችን ኢየሱስ
በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በልባችን መኖሩ ነው፡፡ ይህ ነው እውነተኛ ሃይማኖት፡፡ በሃይማኖት መኖራችንን የምናረጋግጠው በዚህ ነው፡፡
በሃይማኖት
ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ
አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5
ዋና
ያልሆኑ ለክርስትና የማይጠቅሙ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ከእነዚያ ክርክር እንድንሸሽ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
ወደ
መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ
ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት
አይጠቅሙም። 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡3-4
ዋና
ያልሆኑ ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ ዋናው ነገር ግን ኢየሱስ ስለሃጢያታችን መሞቱና በሶስተኛው ቀን መነሳቱ ነው፡፡ የኢየሱስ መሞት ለእኔ
ነው ብሎ ማመንና ኢየሱስን የህይወት ጌታ አድርጎ መከተል ዋና ነገር ነው፡፡
ዋና
ያልሆኑ ነገሮች ክርክር ያመጣሉ እንጂ ለእምነት አይጠቅሙም፡፡ ዋና ነገሮች በየእለቱ የክርስትና ህይወታችሁ ላይ ምንም የሚጨምሩት
ጠቅም የለም፡፡ ዋና ያለሆኑ ነገሮች ለእለት ተእለት የክርስትና ህይወታችሁ ጉልበትን አይሰጡም፡፡ ዋና ያልሆኑ ነገሮች ጉልበትን
ያዳክማሉ፡፡
ሰይጣንም
የሚፈልገው ዋና ባልሆኑ ነገሮች ላይ እንድንጣላና ዋናውን ነገር እንድንረሳው ነው፡፡ ሰይጣንም የሚፈልገው በሚያድነው በኢየሱስ አዳኝነት
ወንጌል ላይ እንዳናተኩርና በአማላጅነትና በስግደት በመሳሰሉት ነገሮች ላይ ጊዜያችንን እንድናባክን ነው፡፡
ዋናው
ነገር የሃይማኖትን ስርአትና ወግ መፈፀም ሳይሆን የልብ መለወጥ ነው፡፡
በክርስቶስ
ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ገላትያ 5፡6
በግልጥ
አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና፥ በግልጥ በሥጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና፤ ዳሩ ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ
ነው፥ መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም፤ የእርሱ ምስጋና ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው
አይደለም። ሮሜ 2፡28-29
ሰው
ቢቀበለውም ባይቀበለውም በህይወት ያን ያህል ለውጥ የማያመጣ ነገር አለ፡፡ ሰው ግን እንዲቀበለው የተገባ ነገር ደግሞ አለ፡፡
ኃጢአተኞችን
ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1:15
ሰው
ቢቀበለው የእግዚአብሄር ልጅ የሚሆንበት ባይቀበለው ደግሞ የእግዚአብሄር ልጅ የማይሆንበትና ለዘላለም ከእግዚአብሄር የሚለያይበት
ትምህርት አለ፡፡
ለተቀበሉት
ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
በልጁ
የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ
3፡36
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #መላእክት #ስግደት #በክርስቶስ #መንፈስ
#ሃይማኖት #ድንግል #ማርያም #የእግዚአብሄርልጅ #ክብር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ማየት
#የእግዚአብሄርመንግስት
#መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ #ማእረግ #ስልጣን #ከፍታ
No comments:
Post a Comment