Popular Posts

Thursday, March 15, 2018

ዝግተኛ መንፈስ

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እግዚአብሄር ፍጥን ፍጥን የሚልን ሰው አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄርነ ቅድም ቅድም የሚልን ሰው አያስደስተውም፡፡ እግዚአብሄር ከእርሱ የሚቀድመውን ሰው አይደሰትበትም፡፡ እግዚአብሄር የእርሱን እርምጃ የማይታገሰውን ሰው አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር እርምጃውን የሚታገስ ሰውን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገውንና እርሱን ለመከተል ዘግየት የሚልን ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የማይቸኩልን ሰው ይፈልጋል፡፡   
በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ 13፡11
የእግዚአብሄር ሰው ኬኔት ሃገን ሲናገሩ እግዚአብሄር አንድ ጊዜ አንዲህ ብለ ተናገረኝ ይላሉ፡፡ እግዚአብሄር እባክህ ልጄ አትቅደመኝ አለኝ ይላሉ፡፡ ከቀደምከኝ ልትከተልኝ አትችልም፡፡ ከእኔ እኩል መራመድ ካልቻልክ እንኳን ዘግየት ብትልም ከኋላዬ  ተከተለኝ፡፡  ከኋላዬ ከሆንክ እኔን መከተል ትችላለህ አለኝ ብለው ይናገራሉ፡፡
እግዚአብሄር ዝግተኛን መንፈስን የሚፈልገው በእርሱ የሚመራን እንጂ ራሱን በራሱ የሚመራን ሰው ስለማይፈልግ ነው፡፡ እግዚአብሄር ዝግተኛ መንፈስን የሚፈልግ ራሱ ለራሱ ጌታ የሆነን ሰው ስለማይፈልግ ነው፡፡ እግዚአብሄር ዝግተኛ መንፈስን የሚፈልገው እግዚአብሄርን መከተል እንዲችል ነው፡፡ እግዚአብሄር ዝግተኛ መንፈስን የሚፈልገው እግዚአብሄር የሚመራውን ሰው ስለሚፈልግ ነው፡፡
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ የሚለው፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። ምሳሌ 3፡5-6
ስለዚህ ነው መጽፅሃፍ ቅዱስ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ የሚለው፡፡ እርፍ ብሎ በፀጥታ እግዚአብሄርን የሚከተል ሰው ይድናል፡፡
ሰው ቸኩሎ እግዚአብሄርን ሳይሰማ ከሚያደርገው መቶ ስራ ይልቅ በዝግታ እግዚአብሄርን ጠብቆና ሰምቶ የሚያደርገው አንድ ነገር ይበልጥ ፍሬያማ ያደርጋል፡፡  
በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡ ኢሳይያስ 30:15
የመታዘዝ ፍሬያማነት ያለው የእግዚአብሄርን ድምፅ ሰምቶ በማድረግ ላይ እንጂ በራስ ማስተዋል ገምቶ በማድረግ ላይ አይደለም፡፡
እግዚአብሄር ያላለንን ገምቶ ከማድረግ እግዚአብሄር ያለንን እያደረግን የእግዚአብሄርን ድምፅ መጠበቅ ይሻላል፡፡ እግዚአብሄር ሳይናገር ፈጥኖ ከመሄድ እግዚአብሄር ከተናገረ በኋላ ፈጥኖ ማድረግ ይሻላል፡፡ እግዚአብሄርን የሚቀድመው እንደሌለ ሁሉ ይመስላል እንጂ እግዚአብሄር እስኪናገር ጠብቆ የሚታዘዘውን ማንም አይቀድመውም፡፡  
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1 ጴጥሮስ 34
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ባህሪ #ፍቅር #ልብ #የዋህ #ዝግተኛ #የመንፈስፍሬ #ውበት #የልብሰው #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment