Popular Posts

Thursday, March 8, 2018

ለውድድር ተጠርተናል

ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል። ማቴዎስ 2312
እግዚአብሄር ለእርሱ ያልፈጠረን ፉክክር አለ፡፡ ነገር ግን ውድድር ሁሉ ክፉ አይደለም፡፡ መልካመ የሆነ ውድድር አለ፡፡ ሰው መወዳደር ከፈለገ በመልካም በመወዳደር ከእግዚአብሄር ሽልማትን ይቀበላል፡፡
ክርስትና የሰነፎች መንግስት አይደለም፡፡ ክርስትና የትጉሆች መንግስት ነው፡፡ ክርስትና ነገሮችን ለመለወጥ የሚሰሩ ሰዎች መንግስት እንጂ ቁጭ ብለው የሚሆነውን የሚያዩ ሰዎች መንግስት አይደለም፡፡
ለከንቱ ለአለም ሃላፊና ጠፊ ሃበትና ዝና አንጋደልም እንጂ በጠበበው ደጅ ለመግባት እንጋደላለን፡፡
በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ማቴዎስ 7፡13
ክርስትና በክፉ የመሸነፍ መንግስት አይደለም እንጂ በመልካም የማሸነፍ የውድድር መንግስት ነው፡፡ 
ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። ሮሜ 12፡21
በክርስትና ንፋስን ነፋስን እንደሚጎስም ሰው እንጋደልም እንጂ በአላማ እንጋደላለን፡፡ 
ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡26
በክርስትና በማየት አንዋጋም እንጂ በእምነት እንጋደላለን፡፡
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12
በክርስትና ለስልጣን ጥቅም አንወዳደርም እንጂ ሌሎችን ለማገልግል እንወዳደራለን፡፡
በክርስትና ለመከባበር ለመናናቅ አንቸኩልም እንጂ ለመከባበር እንሽቀዳማለን፡፡ ተሽቀዳደሙ 
እርስ በርሳችሁ ለመከባበርም ተሽቀዳደሙ (አዲሱ መደበኛው ትርጉም) ሮሜ 12:10
በትእቢት እንሽቀዳደምም እንጂ ለትህትና እንሽቀዳደማለን፡፡
ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ፊልጵስዩስ 2፡2
በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡34
ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል። ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል። ማቴዎስ 23፡11-12
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አክሊል #ሽልማት #ትንሳኤ #ሰማይ #የማይጠፋአከሊል #ትህትና #መልካምነት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ውድድር #ፉክክር #ዋጋ 

No comments:

Post a Comment