Popular Posts

Thursday, March 1, 2018

ወደ ዕረፍቱ ለመግባት

እግዚአብሄር ለሰው የሚያስፈልገውን ማንኛውም ነገር በአምስት ቀን ፈጠረ፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በስድስተኛ ቀን ፈጠረው፡፡ ሰው በስድስተኛው ቀን የተፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር በሰባተኛው ቀን አንዲያርፍ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሰውን ረብሻ አይፈልገውም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን መናወጥና መጨነቅ አይፈልገውም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው የሰውን እረፍት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ሰው እንዲያርፍ ነው፡፡ እግዚአብሄር በዘመናት መካከል የሚናገረው ሰውን ለማሳረፍ ነው፡፡
ሰው የሚያርፈው በእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ሰው የተሰራውና የተነደፈው በእግዚአብሄር ውስጥ እንዲያርፍ ነው፡፡ ሰው በተለያዩ ነገሮች ሊያርፍ አይችልም፡፡ ሰው በእውነት ሊያርፍ የሚችለው በእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰውን የሚያሳርፈው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
ሰው በእግዚአብሄር ክብር ስለተፈጠረ እረፍት ይሰጡኛል ብሎ የሚፈልጋቸው ሃያልነት ፣ ባለጠግነትና ጥበብ አንዳቸውም ነገሮች ሊያሳርፉት አይችሉም፡፡
ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማና በቃሉ ሲኖር ያርፋል፡፡
ሰው የሚያርፈው በራሱ መንገድ አይደለም፡፡ ሰው የሚያርፈው በራሱ ሃይል አይደለም፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሄር ሊያርፍ ይችላል፡፡ እረፍትን ላርፍ አልችልም ብሎ ማንም መፍራት የለበትም፡፡
እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ተስፋ ገና ቀርቶልን ከሆነ፥ ምናልባት ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ እንፍራ። ዕብራውያን 42
እኛ እንድናርፍ የአካባቢያችን መናወጥ መቆም የለበትም፡፡ እኛ ካረፍን አረፍን ነው፡፡ እውነተኛ እረፍት የምድር መነዋወጥና ተራሮች ወደባህር ልብ መወሰድ አይረብሸውም፡፡
ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም። መዝሙር 46፡2
ሰው የሚያርፈው በእምነት ነው፡፡ ከእምነት ውጭ የሚያሳርፍ ምንም ነገር የለም፡፡ ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ዕብራውያን 4፡2
ከእግዚአብሄር ውጭ እረፍት የሚታሰብ አይደለም፡፡ ካለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡
ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። ዕብራውያን 43
የእግዚአብሄርን ቃል መታዘዝ ወደ እግዚአብሄር እረፍት ለመግባት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ አለመታዘዝ ደግሞ ወደ እግዚአብሄር እረፍት ለመግባት ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡
እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ፦ ዕብራውያን 46
አሁን ያለን እርፍት የመጨረሻው የእረፍት ደረጃ አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ባወቅንና በታዘዝን መጠን እረፍታችን እየበዛ ይመጣል፡፡ ይህ ሁሉ እረፍት አለ እንዴ አስከምንል ድረስ በእግዚአብሄር እረፍት እርፍ እንላለን፡፡
እረፍት በእግዚአብሄር ቃል ትጋትን ይጠይቃል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል መስማትና መታዘዝ ተለማምደን የማናውቅው እርፍት ውስጥ ይከተናል፡፡  
እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ። ዕብራውያን 411
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #መታዘዝ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment