Popular Posts

Thursday, March 15, 2018

የዋህ መንፈስ

ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4
በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋው እጅግ የከበረ የልብ ውበት ተብሎ የተጠቀሰው የዋህነት ነው፡፡ የልብ የዋህነት ክፋትን ለማድረግ ሃይል እያለ ሃይልን ለክፋት ላለመጠቀም መወሰን ነው፡፡
በመኸፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ዳንኤል የንጉሱን አትፀልዩ የሚለውን ህግ ተላልፎ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ሲጣል በጉድጓድ ውስጥ የነበሩት እንበሳች ዳንኤልን ለመቦጫጨቅ ሙሉ ሃይል ነበራቸው፡፡ ነገር ግን አንበሶቹ ሃይላቸውን ዳንኤልን ለመቦጫጨቅ ለክፋት አልተቀሙበትም፡፡ አንበሶቹ ክፋት ለማድረግ ሃይል እያለው ነገር ግን ሃይሉን ለመልካም እንጂ ለክፋት ላለመጠቀም የወሰነ ሰው ምሳሌዎች ናቸው፡፡
የዋህ ሰው አስጊ ሰው አይደለም፡፡ የዋህ ሰው ተንኮለኛ ሰው አይደለም፡፡ የዋህ ሰው የሚለውና የሚያስበው አንድ ነው፡፡ የዋህ ሰው ልንደገፍበት የምንችል ሰው ነው፡፡ የዋህ ሰው ልቡ ንፁህ ነው፡፡ የዋህ ሰው ተማምኖ ከእርሱ ጋረ የተቀመጠን ሰው አይጎዳም፡፡ የዋህ ሰው ሃይል ማግኘቱን ብቻ ሳይሆን ሃይሉን ለክፋት ላለመጠቀም ይጠነቀቃል፡፡
በወዳጅህ ላይ ክፉ አትሥራ፥ እርሱ ተማምኖ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ። ምሳሌ 3፡29
የዋህ ሰው ሃይል ብርቁ አይደለም፡፡ የዋህ ሰው ሃይል እንደሌለው አያስብም፡፡ የዋህ ሰው ሃያል እንደሆነ እርግጠኛ ነው፡፡ የዋህ ሰው ሃይሉን በሰው ላይ አይሞክርም፡፡ የዋህ ሰው ሃይሉን በሰው ላይ ለማሳየት አይፈልግም፡፡  
የዋህ ሰው ራሱን ይገዛል፡፡ የዋህ ሰው ራሱን ይቆጣጠራል፡፡ የዋህነት ሞኝነት አይደለም፡፡ የዋህነት አዋቂነት ብልህነት ነው፡፡   
ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። ምሳሌ 16፡32
የዋህ ሰው ርህሩህ ነው፡፡ የዋህ ሰው አዛኝ ነው፡፡ የዋህ ሰው ሃላፊነት ይሰማዋል፡፡ የዋህ ሰው የዝቅተኝነት ስሜት ችግር የለበትም፡፡
የዋህ ሰው አማኝ ነው፡፡ የዋህ ሰው እግዚአብሄርንና ሰውን ያምናል፡፡ የዋህ ሰው እግዚአብሄርንና ሰውን ይወዳል፡፡ የዋህ ሰው የራሱን አይፈልግም፡፡ የዋህ ሰው የሚፈራው ነገር የለም፡፡ የዋህ ሰው የሚደብቀው ህይወት የለውም፡፡ የዋህ ሰው ድብቅ አጀንዳ የለውም፡፡ የዋህ ሰው የተገለጠ ነው፡፡
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1 ጴጥሮስ 34
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ባህሪ #ፍቅር #ልብ #የዋህ #ዝግተኛ #የመንፈስፍሬ #ውበት #የልብሰው #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment