እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለእረፍት ነው፡፡
እግዚአብሄር ለሰው የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አምስት ቀን ከፈጠረ በኋላ በስድስተኛው ቀን ሰውን ፈጠረው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን
የፈጠረው በሰባተኛው ቀን ከማረፉ በፊት በስድስተኛው ቀን ነበር፡፡
እግዚአብሄር ሰውን በክብሩ ስለፈጠረው ሰው በእግዚአብሄር
እንጂ በምንም ነገር ሊያርፍ አይችልም፡፡
ሰው በሃብት ፣ በጥበብና በሃይል እረፍትን ማግኘት
አይችልም፡፡
እረፍት ማለት ደግሞ ሆሊዴይ መውጣት ማለት አይደለም፡፡
እረፍት ማለት ተግዳሮትን አለማየት አይደለም፡፡ እረፍት ማለት የአለም ገንዘብን ሁሉ ማግኘት ማለት አይደለም፡፡ እርፍት ማለት የምንፈልገው
ነገር ሁሉ ሲሆንልን ማለት አይደለም፡፡ እረፍት ማለት ችግር እያለ በችግር ውስጥ አለመናወጥ ማለት ነው፡፡ እረፍት ማለት በተግዳሮት
ውስጥ በፀጥታ መኖር ማለት ነው፡፡
እረፍት በእምነት እንጂ በማየት አይመጣም፡፡ ሰው
የሚያርፍው በእግዚአብሄር ሲያምን ብቻ ነው፡፡
አረፍትን የምናጣጠመው መቼ ነው
1.
እግዚአብሄር የፈጠረን ለራሱ
መሆኑን ስንረዳ ነው
እኛ ራሳችንን አልፈጠርንም
፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለራሱ ፈጥሮናል፡፡ እኛ የራሳችን አይደለንም፡፡ እኛ ሌላ ባለቤት አለን፡፡ ባለቤታችን እግዚአብሄር ነው፡፡ እኛ ለራሳችን ከምናስበው በላይ እርሱ ስለእኛ ያስባል፡፡
በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡20
2.
እኛ ከምንፈልግው በላይ እግዚአብሄር
እኛን ሊመራን እንደሚፈልግ ስንረዳ ነው፡፡
እግዚአብሄር የፈጠረን
ለአላማው ነው፡፡ እግዚአብሄር በራሱ መንገድ እንዲመራን እንፈልጋለን፡፡ እኛ ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር በራሱ መንገድ ሊመራን
ይፈልጋል፡፡
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። ዮሃንሰ 10፡11
3.
እግዚአብሄር ስለእኛ ግድ እንደሚለው
ስንረዳ እናርፋለን
እግዚአብሄር ስለ አንዳንድ
ነገራችን ብቻ ሳይሆን ስለሁሉም ነገራችን ግድ ይለዋል፡፡ እግዚአብሄር ስለዚህም ነገሬ ግድ ይለዋል? ብለን እስከምንገረም ድርስ
ስለዝርዝር የህይወት ጉዳያችን ግድ ይለዋል፡፡
አምስት ድንቢጦች በአሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም። ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ጠጕር ሁሉ እንኳ የተቈጠረ ነው፤ እንግዲያስ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ። ሉቃስ 12፡6-7
4.
እግዚአብሄር ለእኛ መልካም
አላማ እንዳለው ስናውቅ እናርፋለን
እግዚአብሄር እኛን
ከመፍጠሩ በፊት ምን እንደምንሰራ አስቦ ፈጥሮናል፡፡ በምድር የተፈጠርነው ልንሰራው ያለ ስራ ስለነበር ነው፡፡ እግዚአብሄር የህይወታችንን
መጨረሻ ከመጀመሪያው ያውቀዋል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታቸን ላይ ያለው አላማ ፍቅር ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርምያስ 29፡11
5.
እንግዶች እንደ ሆንንና ቤታችን
በሰማይ እንደሆነ ስናውቅ ነው
እንግዶችና መጻተኞች
እንደሆንን ይህች ምድር እያለፍንባት እንጂ አገራችን እንዳልሆነች አገራችን በሰማይ እንደሆነ ስናስታውስ እናርፋለን፡፡ እንግዶች
እንደሆንን ስንረዳ ከአለም ክፉ ፉክከር ራሳችንን እናገላለን እረፍትም ውስጥ እንገባለን፡፡
ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡11
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት
#መታዘዝ #ሰማይ #ምሪት #እንግዶች #መጻተኞች #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት
#መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment