Popular Posts

Follow by Email

Monday, March 12, 2018

ለልብ ጥንካሬ ፍቱን መድሃኒት


የልብ ጥንካሬ ሰውን ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ያበላሻል፡፡ የልብ ጥንካሬ ሰው ከራሱ ጋረ ያውን ግንኙነት ይበክላል፡፡ የልብ ጥንካሬ ሰው ከሰው ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠፋል፡፡
እግዚአብሄር ከሰው ጋር እንደ ልቡ እንዳይፈስ የሚያግደው የሰው ልብ ጥንካሬ ነው፡፡
የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል? ኤርምያስ 17፡9
ልብ የህይወት መውጫ ነው፡፡ ልብህ ከተበላሸ ሁሉም ነገርህ ተበላሸ፡፡
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። ምሳሌ 4፡23
መፍትሄ የሌለው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን፡፡ ለልብ ጥንካሬ መፍትሄ ባይኖረው ኖሮ ምን ይውጠን ነበር? ለልብ ጥንካሬም መፍትሄ አለው፡፡
እግዚአብሄር ከሰው ጋር ያለውን ግንኙነት ሲያድስ ያደሰው የሰውን ልብ ነው፡፡
አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። ሕዝቅኤል 36፡26
የሰው ልብ በጣም በጥንቃቄ መያዝ ያለበት በጣም አታላይ ነው፡፡
የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል? ኤርሚያስ 17፡9
የሰው ልብ ጠንካራ እንዳይኖረው መንፈስ ቅዱስ ወሳኝ ቦታ አለው፡፡
አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። ሕዝቅኤል 36፡26
የሰው ልብ ጠንካራ እንዳይሆን መዶሻ የሆነው የእግዚአብሄር ቃል ይጠይቃል፡፡
በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርሚያስ 23፡29
የቅዱሳን ህብረት የወንድሞች ልብ እንዳይጠነክር ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ ዕብራውያን 3፡12-13
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #ልብ #የልብጥንካሬ #ንስሀ #መመለስ ##መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment