Popular Posts

Sunday, March 18, 2018

ዓይኖቼን ክፈት

ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ። መዝሙር 119፡18
አይን በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ አይንህ ጤናማ ከሆነና በትክክል ካየህ ሁሉም የህይወትህ ጤናማ ይሆናል፡፡ አይንህ በትክክል ካላየ ግን ህይወትህ ሁሉ ጨለማ ይሆናል፡፡ የህይወት ስኬትህ የሚለካው አይንህ በተከፈተና እንደ እይታህ በተመላለስክ ልክ ብቻ ነው፡፡
የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ማቴዎስ 6፡22
አይናችን ሲከፈት ከአካባቢያችንብ አሻቅበን ማየት እንችላለን፡፡
አይናችን ካልተከፈተ እግዚአብሄር በክርስቶስ ያዘጋጀልንን በረከት ማየት አንችልም፡፡ አይናችን ካልተከፈተ በዙሪያችን ያሉትን ተግዳሮቶች ብቻ አይተን እንደክማለን፡፡
አይናችን ሲከፈት ነገሮችን የምንተረጉምበት አተረጓጎም ይለያል፡፡
ሙሴ ከንአንን እንዲሰልሉ የላካቸው ሰላዮች አብዛኞቹ ከሚኖሩባት ሰዎች ታላቅነት የተነሳ እኛ በእነርሱ ፊት እንደ አንበጣ ነን ብለው ሲናገሩ ካሌብና ኢያሱ ግን ከግዙፍነታቸው የተረዱት ነገር የሚበሉትን እንጀራ ታላቅ እንደሆነ ብቻ እንጂ የከነአናዊያንን ታላቅነት  አልነበረም፡፡  
እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው። ዘኍልቍ 14፡8-9
አይናችን ሲከፈት ከችግሮች ውስጥ እድልን እናያለን፡፡ አይናችን ካልተከፈተ በከንቱ እንራወጣለን ህይወታችንን በከንቱ እናባክናለን፡፡አይኑ የተከፈተው ነቢዩ ኤልሳ ከተግዳሮቶቹ መካከል እድሎቹን እንዲያይ የብላቴናው አይን እንዲከፈትና ፀለየ፡፡ ብላቴናው አይኑ ሲከፈት ከከበቡት የሰው ጠላቶች ባሻገር ያጀቡትን የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ማየት ቻለ፡፡   
እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው። ኤልሳዕም፦ አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር። 2ኛ ነገሥት 6፡16-17
አይናችን ሲከፈት በድካም ውስጥ ብርታትን እናያለን፡፡
ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡10
አይናችን ሲከፈት ዱለት ነው ከሚሉት ጋር አብረን ዱለት ነው አንልም፡፡
ይህ ሕዝብ፦ ዱለት ነው በሚሉት ሁሉ፦ ዱለት ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፥ አትደንግጡ። ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን። ኢሳያስ 8፡12-3
ፀሎት
እግዚአብሄር ሆይ ስለአባትነትህ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ አይኖቼን ክፈት፡፡ እግዚአብሄር ሆይ አንተ በክርስቶስ ያደረክልኝን ሁሉ መረዳት እንድችል  የጥበብና የመገለጥን መንፈስ ስጠኝ፡፡ ከተግዳሮት ውስጥ ወርቃማ እድሎችን ማየት እችል ዘንድ አይኔን ክፈት፡፡ ከአንት ጋር በትክክል መራመድ እንድችል አንተ ስለህይወቴ የምታየውን ሁሉ ልይ፡፡ አይኔን ስለምትከፍት ተኣምራትን ሰለማይ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #አይን #እይታ #ተኣምራት #እድል #ዘመን #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ይሳኮር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment