Popular Posts

Tuesday, March 27, 2018

የአፅናኙ መንፈስ ቅዱስ አምስት እጥፍ በረከቶች

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ (አፅናኝ ፣ ተሟጋች ፣ የሚማልድ አማካሪ ፣ አብሮ የሚቆም ) እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ  14:26
ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ እንደአባት ነበር፡፡ እንደአባት ይመራቸዋል ያስተምራቸዋል ይመክራቸዋል፡፡ ኢየሱስ በምድር በነበረ ጊዜ ስጋ ለብ ስለመጣ ውስን በመሆኑ ይህንን ሊያደርግ የቻለው ለደቀመዛሙርቱ ብቻ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከምድር ላይ ሲወሰድ ደቀመዛሙርቱን አባት እንደሌላቸው ልጆች እንደማይተዋቸውና አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣና እንደሚመራቸው ይነግራቸው ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ እና በአማኙ ውስጥ ሲኖር የሚያደርጋቸውን አምስት ነገሮችን እንመልከት፡፡
1.      አፅናኝ
ኢየሱስን ስንቀበል እና መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሲኖር የሚያደርገው ነገር እኛን ማፅናናተ ነው፡፡ ማፅናናተ ማለት ደግሞ ህይወታቸንነ ማመቻቸት የተመቻቸ ሁኔታን መፍጠር የሚቆረቁረንን ነገር ማወገድ እንቅፋትን ከፊታችን ማስወገድ ማጽፅናናት ደስ ማሰኘትና በደስታ እና በስኬት ጌታን እንድንከተል ማስቻል የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነው፡፡
ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ ዮሃንስ 14፡15-16
2.     ተሟጋች
መንፈስ ቅዱስ ጠበቃችን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ወገን ሆኖ ነገሮችን እና ሁኔታዎችን እንዴት እንደምናልፍ ይቆምልናል፡፡ እኛ መናገር ባልቻልን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አፋችንን ተጠቀሞ ይናገርልናል፡፡ በህይወት ሁኔተ ውስጥጭ በተግዳሮት ውስጥ የእኛ ወገን ሆኖ ምን ማድረግ እንዳለብን እንደጠበቃ ያማክረናል ይመራናል፡፡
አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና። ማቴዎስ 10፡19-20
3.     የሚማልድ
መንፈስ ቅዱስ ምን መፀለይ እንዳለብን በማናውቅበት ጊዜ እንኳን ያለማወቅ ድካችንን ያግዛል፡፡ ፀሎታችን ከንቱ አንዳይሆን ይረዳል፡፡ ፀሎታችን የእግዚአብሄርን ልብ ያማከለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ጸሎታችን ፍሬያማ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ሮሜ 8፡26
4.     አማካሪ
ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ድንቅ መካር ነበር፡፡ አሁን መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ድንቅ መካር ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚመክረው ምክር መሬት ጠብ የማይል ምክር ነው፡፡
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሃንስ 2፡27
5.     አብሮ የሚቆም
መንፈስ ቅዱስ ሁሌ አብሮን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን ለዘላለም ከእኛ ጋር አብሮ እንዲኖር ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አልነበረም ብለምን የምናመካኝበት ጊዜ የለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በየጊዜው አይጎበኘንም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ይኖራል፡፡  
ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም። ሐዋሪያት 6፡10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #የሚማልድ #አማካሪ #ተሟጋች #ጠበቃ #እውነት #በውስጣችሁ #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment