አንዳንድ ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉ አቅደው ጨርሰው
እግዚአብሄር ጋር ይመጡና ይኸው አቅጄልሃለሁ ተጨመርበት ይሉታል፡፡ እግዚአብሄርን እንደ ህይወታቸው ባለቤት ሳይሆን እንደ ተጨማሪ
ጉልበት ያዩታል፡፡ እግዚአብሄርን እንደ ዋና ሳይሆን እንደ ተጠባበቂ ይቆጥሩታል፡፡
በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ
በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡20
እግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን
ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር የህይወታችን ባለቤት ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠራን ለራሱ ነው፡፡
ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር
ዳርቻ፥ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። ኢሳያስ 43፡7
ብዙ ሰዎች እግዚአብሄርን የሚፈልጉት የህይወታቸውን
እቅድ እንዲሰጣቸው አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልጉት ለምን እንደጠራቸው ለማወቅ አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልጉት ለምን
እንደጠራቸው ፈልገው ለማግኘት አይደለም፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልጉት እርሱ ለእነርሱ ያለውን ዘላለማዊ እቅድ ለማግኘት አይደለም፡፡
እርሱን የሚፈልጉት ወደምድር የተፈጠሩበትን ልዩ አላማ ለማግኘት አይደለም፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤
ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርምያስ 29፡11
እግዚአብሄርን የሚፈልጕት የራሳቸውን መንገድ ከሄዱ
በኋላ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በራሳቸው መንገድ ከተሳካላቸው ተመልሰው አይመጡም፡፡ የራሳቸውን መንገድ ሲሄዱ ካልተሳካላቸው ለእርዳታ
ወደ እግዚአብሄር ይመጣሉ፡፡ ወደ እግዚአብሄ የሚመጡት የራሳቸውን አቅድ ትተው የእርሱን አቅድ ለመፈለግ አይደለም፡፡ ወደ እግዚአብሄር
የሚመጡት እርሱ አስቀድሞ ለህይወታችው እቅድ እንደነበረው ስለተረዱ አይደለም፡፡ ወደ እግዚአብሄር የሚመጡት የሚፈልጉት አላማቸውን
ለማስፈፀም የሚረዳቸውን እርዳታ ብቻ ፈልገው ነው፡፡
የምንፀልየው ለእግዚአብሄር እቅድ ለመስጠት ሳይሆን
እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን እቅድ ለመቀበልና ከእርሱ ጋር ለመተባበር ነው፡፡
እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርምያስ 29፡12-13
እግዚአብሄር የሚጠብቀው ምን እንደሚሰሩለት እንደሚፈልግ
እንዲጠይቁት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው የህይወታችውን እቅድ እንዲጠይቁት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሄር
ስፖንሰር የሚደረገውን የእርሱን አላማ እንዲፈልጉ ነው፡፡
የምትፈልጉበት ቦታ እየሄዳችሁ እግዚአብሄን መንገድ
ላይ ፌርማታ ላይ ልታሳፍሩት አትፈልጉ፡፡ እግዚአብሄ እናንት የምትሄደፉት ለመሄድ ፍላጎት የለውም፡፡ እግዚአብሄር የሚሄድበትን ያውቃል፡፡
እግዚአብሄር የሚሄድበትን እንድትመርጡለት አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ከእርሱ ጋር እርሱ የሚሄድበት እንድትሄዱ ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው እርሱ የሚሄድበት ተከትላችሁት አብራችሁ እንድትሄዱ ነው ፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ እቅድ እንድትገቡ እንጂ
የሚፈልገው በእቅዳችሁ ውስጥ እንድታስገቡት አይደለም፡፡
እግዚአብሄር የእቅድ የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር
ትጉህ ሰራተኛ ነው፡፡ በክርስትና ስራ ፈጣሪዎች መሆን አይጠበቅብንም፡፡ ከእርሱ ጋር ከሰራን ይበቃል፡፡ እርሱ በህይወታችን የሚሰራውን
ተረድቶ ከመተባበር በላይ የህይወትና የአገልግሎት ስኬት የለም፡፡
ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ዮሃንስ 5፡17
የእግዚአብሄርን ፈቃድ ፈልጎ ከመከተል የተሻለ
ፈጣሪነት የለም፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ አግኝቶ ከመከተል በላይ ጥበብ የለም፡፡
ሰው ግራ የሚጋባውና የሚሸወደው ለአገዚአብሀር
እቅድ ለማውጣት ሲሞክር ነው፡፡ ለአግዚአብሄር አቅድ የሚያወጣ ሰው የሚፈፅመው በራሱ ወጪ እንጂ በእግዚአብሄር አይደለም፡፡ ሰው
ህይወቱን ውስብሰብ የሚያደርገው ለእግዚአብሄር አዳዲስ ሃሳቦችን አምጥቶ ሊያስፈፅም ሲሞክር ነው፡፡ ያንተን የተሻለ ሃሳብ ተውና
የእግዚአብሄርን እቅድ ፈልግ፡፡
ሰው ግን የእግዚአብሄርን ፈቃድ አውቆ ማድረግ
ከፈለገ ማወቅ ይችላል በዚያም ይከናወንለታል፡፡
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል። ዮሃንስ 7፡17
ከሰው
ጥበብ ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባል፡፡
ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡25
የሰው
የረቀቀ ጥብብ ሊደገፉበት የሚበቃ አይደለም፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥
እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። ምሳሌ 3፡5-6
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት
#መደገፍ #ሰንበት
#ማረፍ #ፅድቁን
#ኢየሱስ #ክርስቶስ
#ጌታ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #መታመን
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment