Popular Posts

Wednesday, March 7, 2018

አራቱ የኢየሱስ የአለባበስ ደረጃዎች

ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም። እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? ማቴዎስ 6፡28-30
ኢየሱስ ምን እንለብሳለብ ብላችሁ አትጨነቁ የሚል ነበር መልክቱ፡፡ ኢየሱስ እኛ ልጆቹን አግዚአብሄር እንዴት እንደሚያለብሰን ያስተምር ነበር፡፡
ኢየሱስ በትምህርቱ አራት የአለባበስ ደረጃዎችን ጠቅሶ አልፎዋል፡፡
አራተኛው የአለባበስ ደረጃ የተራ ሰው የአለባበስ ደረጃ ነው፡፡
እንደ ሰለሞን የማይለብሱ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡
ሶስተኛው የአለባበስ ደረጃ የንጉስ ሰለሞን የአለባበስ ደረጃ ነው፡፡
ንጉስ ሰለሞን ከማንም ሰው የተሻለ ይለብስ ነበር፡
. . . ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም። ማቴዎስ 6፡29
ሁለተኛው የአለባበስ ደረጃ የአበቦች የአለባበስ ደረጃ ነው፡፡
ስለአበቦች አለባበስ ሲናገር ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም ይለናል፡፡
የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም ማቴዎስ 6፡28-29
አንደኛው አለባበስ የእኛ አለባበስ ደረጃ ነው፡፡
ስለእኛ አለባበስ ደረጃ ሲናገር ከአበቦች ከፍ ያለ የአለባበስ ደረጃ እንደምንለብስ ይናገራል፡፡
እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? ማቴዎስ 6፡29
እግዚአብሄር ይመስገን፡፡
ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም። እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? ማቴዎስ 6፡28-30
እግዚአብሄር 1ኛ ደረጃ እንደሚያለብሰን አውቀን የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቁን እንፈልግ፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31-33
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ሰለሞን #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ድንግል #ማርያም #ኦርቶዶክስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment