Popular Posts

Saturday, March 3, 2018

ለአንዱ ችግር ለሌላው ግን እድል

ጊዜው ቆየት ብሎዋል ይባላል፡፡ የጫማ አምራች ኩባንያ ሁለት የሽያጭ ባለሙያዎች ገቢያውን እንዲያጠኑ ወደ ቻይና ይላካሉ፡፡
አንዱ ሰዉ ጫማ የማድረግ ባህል የለውም ዋጋ የሌለው ነገር ነው ብሎ በተስፋ መቁረጥ ወደላከው ኩባንያ ተመለሰ፡፡
ሌላፃው ደግሞ ይገርማል ጫማ የሚያስፈልጋቸው ጫማ የሌላቸው ብዙ ሰዎች አሉ በፍጥነት ጫማዎች ይላኩና ይሸጡ ብሎ ለኩባንያው ምክርን ይሰጣል፡፡
ሁለቱ የሽያጭ ባለሙያዎች ያዩት አንድ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ያዩትን አንድ ነገር የተረጎሙበት አስተሳሰብ በፍፁም የተለያየ ነው፡፡ ለአንዱ ችግር የሆነው ለሌላው እድል ሆነለት፡፡
በህይወትን እንደዚሁ ነው፡፡ በህይወታችን የሚያልፊ ነገሮች ሁሉ ችግሮች ቢመስሉም ውስጣቸው ግን ታላቅ እድልን ይዘው ይመጣሉ፡፡
ለአንዱ ማጥፋት ለሌላው ማግኘት ነው
ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ማቴዎስ 16፡25
ለአንዱ ድካም ለሌላው ግን ሃይል ነው
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።  ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9-10
ለአንዱ ሃዘን የሆነው ለሌላው ግን ደስታ ነው
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ያዕቆብ 1፡2-3
ለአንዱ ሞኝነት ለሌላው ግን ጥበብ ነው
ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14
ለአንዱ መበተን ለሌላው ግን መዝራት ነው
በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል። 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡8-9
ለአንዱ ድካምና ሞት ነው ለሌላው ፍሬያማነት ነው
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ዮሃንስ 12፡14
ለአንዱ መዋረድ ለሌላው መክበር ነው፡፡
ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል። ማቴዎስ 23፡11-12
ለአንዱ የእንቅፋት ድንጋይ የሆነው ለሌላው ግን ወደከፍታ መወጣጫ ደረጃ ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ዘመን #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ይሳኮር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment