Popular Posts

Monday, March 5, 2018

ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል

ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። ማቴዎስ 12፡30
የሆነ ስራ ብቻ መስራታችን አይበቃም፡፡ የሆነ አገልግሎት ማገልገላችን አይበቃም፡፡ የሆነ ነገር መናገራችን አይበቃም፡፡ የሆነ ነገር ማድረጋችን አይበቃም፡፡
እግዚአብሄር የሃሳብ ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር የስራ ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር የፈጠራ ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር የእቅድ ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር የራእይ ችግር የለበትም፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው የእርሱን እቅድ የሚያስፈጽምን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው እርሱን የሚከተልን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ፈቃዱን የሚታዘዘውን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር ስለ እያንዳንዳችን አቅድ አለው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው የሚልከው ቦታ የሚሄድን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው በራሱ የማይሮጥን ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ፈቃዱን የሚፈልግንና የሚያደርግን ሰው ነው፡፡
እግዚአብሄር ለእርሱ አቅዶለት ጨርሶ ማህተም የሚያስመታው ሰው አይፈልግም፡፡ በራሱ የሚሮጥ በከንቱ ይሮጣል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የማይሰራ በከንቱ ይደክማል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የማይወጣ አያሸንፍም፡፡
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል። መዝሙር 127፡1
እግዚአብሄር የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰራተኛ አምላከ ነው፡፡ እግዚአብሄር ትጉህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይሰራል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የሚሰራ ይከናወናል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የሚሰራ ያሸንፋል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የሚሰራ ይወጣል፡፡
ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ዮሃንስ 5፡17
እግዚአብሄር የሚሰማ ይሳካል፡፡ እግዚአብሄርን የሚታዘዝ ይለማል፡፡ እግዚአብሄርን የሚከተል ይከናወናል፡፡
ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። ማቴዎስ 12፡30
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment