እግዚአብሄር እንድትሰሩ የሰጣችሁን ስራ ለመስራት
ምንም ሃይል አይጎድልባችሁም፡፡ እግዚአብሄር የጠራችሁን ለማድረግ ምንም አታጡም፡፡ እግዚአብሄር ያላችሁ ቦታ ለመድረስ ምንም አቅም
አይጎድልባችሁም፡፡
እግዚአብሄር የጠራችሁ አቅማችሁን ተማምኖ አይደለም፡፡
እግዚአብሄር የጠራችሁ ችሎታችሁን አይቶ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የጠራችሁ ሃይላችሁን አስቦ አይደለም፡፡
እግዚአብሄር የጠራችሁ ሃይሉን ብቻ ተማምኖ ነው፡፡
እግዚአብሄር የጠራችሁ ችሎታውን አይቶ ነው፡፡ እግዚአብሄር የጠራችሁ አቅሙን አይቶ ነው፡፡ እግዚአብሄር የጠራችሁ የሚያስችል ሃይሉን
ፀጋውን ተማምኖ ነው፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ
ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን
በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር
ሁሉ ስለ ሰጠን፥
በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ
እውቀት ጸጋና ሰላም
ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ
1፡2-3
እግዚአብሄር ይህን አድርግ ሲለን ለቀልድ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሲያዘን ከልቡ
ነው፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ አድርግ ካለን ባይመስለንም እንኳን ማድረግ እንችላለን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ያዘዘንን የምንሆነው
ግን በራሳችን ሃይል አይደለም፡፡ አድርጉ ያለንን ለማድረግ የሚያስችለው የእግዚአብሄር ፀጋ ይጠይቃል፡፡ ካለ እግዚአብሄር ሃይል
የእግዚአብሄርን ስራ መስራት አይቻልም፡፡ ካለ እግዚአብሄር ፀጋ ለወንጌል እንደሚገባ መኖር አይቻልም፡፡
እግዚአብሄር እንደዚህ ሁንልኝ ሲለን ከልቡ ነው፡፡ እግዚአብሄር ማድረግ የማንችለውን
ነገር ለማዘዝና ለመቀለድ ፍላጎቱም ጊዜውም የለውም፡፡
እግዚአብሄር ይህ ይኑርህ ሲለን ከልቡ ነው፡፡ ይህ ይኑርህ ያለው ጌታ እንዲኖርህ
የሚያስችል አቅም በውስጥህ አስቀምጧል፡፡
ሃዋሪያው ቅዱሳን ለሆኑ የሚገባውን የህይወት ዘይቤና ከቅዱሳን የሚጠበቀውን ከፍ
ያለ የክርስትና ደረጃ ከዘረዘረ በኋላ እንዴት ይቻላል ለሚለው ጥያቄ እንዲህ በማለት መፍትሄውን ይሰጣል፡፡ ቲቶ 2፡2-10
ለማንኛውም የህይወት ጥያቄ መልስ አለው፡፡ መልስ የሌለው ጥያቄ የለም፡፡ ለማንኛውም
አለመቻል መፍትሄው የእግዚአብሄር ፀጋ ነው፡፡ ለማንኛውም አቅም ማነስ መፍትሄው የሚያስችል ሃይሉ ነው፡፡ ለማንኛውም ብቃት ማነስ
መልሱ የእግዚአብሄር ፀጋ ነው፡፡
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና
ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ
እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ቲቶ 2፡11-13
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ
No comments:
Post a Comment