አንተስ
የአሁድ ንጉሥ ከሆንህ፥ ራስህን አድን እያሉ ይዘብቱበት ነበር። ሉቃስ 23፡37
የሚያልፉትም
ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና። ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥ ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን አሉ። ማርቆስ 15፡29-30
ኢየሱስ ለሃጢያታችን ሊሞት ወደ ምድር ሲመጣ የእኛን
ስጋ ለብሶ ነው፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ በሁሉ ነገር እንደኛ ተፈትኖዋል፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሰቀል ከመስቀል እንዲወርድና
ሃይሉን እንዲያሳይ ተፈትኖዋል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ሃይሉን ከማሳየት ይልቅ ባሀሪን ማሳየት መረጠ፡፡ ኢየሱስ ሃይሉን ከማሳየት
ይልቅ ሃይሉን ላለማሳየት መረጠ፡፡ ኢየሱስ ሃይሉን ለማሳየት ከመስቀል ከመውረድ ይልቅ በመስቀል በመቆየት በትግስት ደህንነታችንን
መፈፀም መረጠ፡፡ ኢየሱስ ሃይሉን ከማሳየት ይልቅ እንደደካማ ተቆጠረ፡፡
ኢየሰስ ሃይሉን በማሳየትከሚገኝ እርካታ ይልቅ
ሃይሉን ላለማሳየት ትህትናን መረጠ፡፡ ኢየሱስ ሃይሉን በማሳየት ዝነኛ ከመሆን ይልቅ በመስቀል የመሞትን ነውርን መረጠ፡፡ ኢየሱስ
ነውርን አክብሮ በመስቀል ላይ ላለመሰቀል ሃይሉን ከማሳየት ይልቅ በመስቀል የመሞትን ነውርን ንቆ በመስቀል ላይ ለመሞት ታገሰ፡፡
ኢየሱስ ራሱን ለማዳን ሳይሆን ሰውን ለማዳን ነው ወደ ምድር የመጣው፡፡ ኢየሱስ ለራሱ ክብር ሳይሆን ሰውን ሊያከብር ነው በመስቀል
ላይ የተዋረደው፡፡
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት
እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2
አሁንም እኛን ለአለም ሞተናል ተሰቅለናል ብለን
ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን ከመስቀል ውረድ እና ሃይልህን አሳየን የሚሉ ብዙ ነገሮች በህይወታችን ያጋጠሙናል፡፡ ስጋችን ፍቀድልኝ
አንዴ ሃይሌን ላሳያቸው ይለናል፡፡
እኛ ግን ሃይላችንን ከማሳየት ይልቅ የእግዚአብሄርን
አላማ በህይወታችን ለመፈፀም መዋረድን እንመርጣለን፡፡ እኛ ሃይላችንን ከማሳየት ይልቅ ለእግዚአብሄር ሃሳብ መሸነፍን እንመርጣለን፡፡
ሃይላችንን አሳይተን በሰው ፊት ጎሽ ከመባል ይልቅ ሃይላችንን ላለማሳየት በመታገስ በእግዚአብሄር ፊት ብቻ ጎሽ መባልን እንመርጣለን፡፡
ሁልጊዜ ከመስቀል ወረድ የሚለውን የፉክክር ጥሪ
እንቢ ባልን መጠን እንደ ስንዴ ቅንጣት ተዘርተን ሞተን ብዙ ፍሬ ማፍራት እንችላለን፡፡
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ዮሃንሰ 12፡24
ከመስቀል ውረድ የሚለውን ሰምተን በታዘዘን መጠን
ስጋችን ሞቶ ለብዙዎች በረከት ለመሆን ያለንን እድል እና ክብር እናባክነዋለን፡፡
የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና።
ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥ ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን አሉ። ማርቆስ 15፡29-30
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ
#ፍቅር #ሰላም
#ስጋ #ምኞት
#ማሰብ #ህይወት
#ሞት #ደስታ
#ዘር #ባህሪ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት
#የዋሃት #ራስንመግዛት
#ትግስት #ትህትና
No comments:
Post a Comment