Popular Posts

Tuesday, March 6, 2018

. . . ለምኑ?!

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡7-8
እውነት እንነጋገርና ከተባለ ፀሎት ስንፀልይ መጀመሪያ ወደ አእምሮዋችን የሚመጣው ምንድነው? ስንፀልይ ወደ አእምሮዋችን የሚመጣው ደሞዛችን ነው፡፡ ስንፀልይ ወደ አእምሮዋችን የሚመጣው የንግዳችን ገቢ ነው፡፡ ስንፀልይ ወደ አእመሮዋችን የሚመጣው የባንክ ሂሳባችን ነው፡፡ ስንፀልይ ወደ አእምሮዋችን የሚመጣው ዝእኛ ማደረግ የምንችለው ነው፡፡  
ለምኑ ማለትት ግን እንደገቢያችሁ መጠን ለምኑ ማለት አይደለም፡፡ ለምኑ ማለተ ግን እንደንግዳችሁ ገቢ መጠን ለምኑ ማለት አይደለም፡፡ ለምኑ ማለት ግን ለምኑ ማለት ነው እንጂ እንደባንክ ሂሳባችሁ መጠን ለምኑ ማለት አይደለም፡፡
ለምኑ ያለው በእናንተ ኪስ ተማምኖ አይደለም፡፡ ለምኑ ያለው የባንክ ሂሳባችሁን ሁኔታ አይቶ አይደለም፡፡ ለምኑ ያለው የንግዳችሁን ገቢ አስልቶት አይደለም፡፡ ለምኑ ያለው የደሞዛችሁን ሁኔታ አውጥቶና አውርዶ አይደለም፡፡
እንዲያውም ለምኑ ያለው በደሞዛችሁ ስላልተማመነ ነው፡፡ ለምኑ ያለው እንደ እግዚአብሄር ልጅ ከንግዳችሁ በላይ መኖር ስላለባችሁ ነው፡፡ ለምኑ ያለው የደሞዛችሁን ውስንነት ስላየ ነው፡፡ ለምኑ ያለው በባንክ ሂሳባችሁ እንዳትወሰኑ ስለፈለገ ነው፡፡
ለምኑ ያለው በራሱ ተማምኖ ነው፡፡ ለምኑ ያለው በሁሉን ቻይነቱ ተማምኖ ነው፡፡ ለምኑ ያለው በራሱ እንጂ በእናንተ ተማምኖ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ለምኑ ያለው በእኛ ነገር ተማምኖ ከሆነ እግዚአብሄርን መለምን ለምን ያስፈጋል? እግዚአብሄር በእኛ ሁኔታ የሚወሰን ከሆነ ከሁሉ የምናንስ ምስኪኖች ነን፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ አቅም በላይ ካልሰራ አምላክነቱ ምኑ ላይ ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛ የማንችለውን ነገር ካላደረገ አምላክነቱ ምኑ ላይ ነው?
እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሞላለት ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛ ልጆቹ እንዳይጎድልብን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በሙላት እንድንኖር ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ከብልፅግናው በቀጣይነት እንድንካፈል ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር እንድንለምን ይፈልጋል፡፡
የመለመን ትልቁ እንቅፋት ልመናን በገቢ መጠን ፣ ልመናን በደሞዝ መጠን ፣ ልመናን በባንክ ሂሳብ መጠን መወሰን ነው፡፡
እግዚአብሄር የሚሰጣችሁ እንደባለጠግነቱ መጠን እንጂ እንደ ባለጠግነታችሁ መጠን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚሰጣችሁ እንደሃብቱ መጠን እንጂ እንደ ሃብታችሁ መጠን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚሰጣችሁ እንደ መዝገቡ መጠን እንጂ እንደ ባንክ ሂሳብ መጠናችሁ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚሰጣችሁ እንደ አሰራሩ መጠን እንጂ እንደ ስራችሁ ደሞዝ መጠን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚሰጣችሁ እንደባለጠግነቱ መጠን እንጂ እንኪሳችሁ መጠን አይደለም፡፡
አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡7-8
ፀሎት
እግዚአብሄር ሆይ አእምሮዬን አስፋ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ በፀሎት ውስጥ ያስቀመጥከውን ታላቅ እድል ማየት እንድችል እርዳኝ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ፀሎትን በእኔ አቅም እንዳልወስነው አይኖቼን ክፈት፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ፀሎትን አንተ እንደምታየው ማየት እችል ዘንድ የልቦናዎቼን አይኖች አብራ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ለምኑ #ፈልጉ #አንኳኩ #ይቀበላል #ያገኛል #ይከፈትለታል #ቃል #ብልፅግና #ሃብት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርቃል  #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment