Popular Posts

Saturday, March 17, 2018

በአንዳች አትጨነቁ

እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡7
በህይወት የሚያስጨንቁ ነገሮች ሲመጡ እንደዚህ ቃል የሚያሳርፍ ነገር የለም፡፡ ይኸው ጥዬዋለሁ ስንል የሆነ ነገር ከላያችን ላይ ውድቅ ይላል፡፡ ምንም ነገር ይሁን ምንም በእርሱ ላይ መጣል ትችላለን፡፡ እርሱ የማይቀበለው ትልቅና ትንሽ ነገር የለም፡፡ እናንተን ካስጨነቃችሁ እርሱ አስቦበታል ማለት ነው፡፡  
የህይወት ሃላፊነት ሲከብድ ፣ በጊዜዬ ማድረግ ያለብኝን ነገሮች አድርጌያለሁ ወይ ብለን ስንጠይቅ ፣ እንደሚገባ ሮጫለሁ የሚሉ ጥያቄዎች በትክክል ካለተመለሱ ያስጨንቃሉ ፊት ከሰጠናቸው እኛን በህይወታችን የመዋጥ ጉልበት አላቸው፡፡
በህይወቴ ስኬታማ ነኝ ወይ ፣ ጊዜዬም በትክክል እየተጠቀምኩ ነው ወይ ፣ በውሳኔያ አልተሳትኩም ወይ ፣ እግዚአብሄር የፈለገው መንገድ ላይ ነኝ ወይ ፣ የሚሉት ጥያቄዎች በእግዚአብሄር ቃል በሚገባ ካልተመለሱ የሚፈጥሩት ጭንቀት አንድን ሃያል ሰው ሽባ አድርጎ የሚያስቀምጥ ትልቅ ሃይል ያለው ነው፡፡
አትጨነቁ ማለት ቸልተኛ ሁኑ ማለት አይደለምን፡፡ አትጨነቁ ማለት ማንም እቅድ አያውጣ ማለት አይደለም፡፡ አትጨነቁ ማለት ከእናንት የተሻለ ነገሮችን ለየሚይዘው ለእግዚአብሄር ስጡት ማለት ነው፡፡
እርሱ ስለ አንተ ያስባል ያቅዳል፡፡ እርሱ ከአንተ በላይ ለአንተ ያስባል፡፡ እርሱ በእውቀትና በማስተዋል ለአንት ያስባል፡፡ አንት ውስን ነህ፡፡ እርሱ ሲያስብ እውቀቱም ችሎታውም ስላለው ይችልበታል፡ ለአንተ ጭንቀት የሚሆነው ለእርሱ እቅድ ነው የሚሆነው፡፡ ለአንተ ጭንቀት የሚሆነው ለእርሱ የዘወትር ስራው ነው፡፡  
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡7
እናንተ ህይወታችንሁ ሁሉ የምትለፉለት ነገር መቅደም ያለበትን ነገር ካስቀደማችሁ እርሱ እንደምርቃርት የሚጨምረው ቀላል ነገር ነው፡፡
ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። ማቴዎስ 6፡32-35
ከህይወት ጭንቀት አንዱም አይገባንም፡፡ ከህይወት ጭንቀት ስንጥርዋም ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን ልትወስድ አይገባም፡፡ ጊዜያችንን ሊወስድ የሚገባው ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ፀሎት ነው፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ፊልጵስዩስ 4፡6
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #ማረፍ #ፀጋ #ፀሎት #ልመና #ምስጋና #ምናን ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment