Popular Posts

Follow by Email

Thursday, April 13, 2017

የክርስቶስ ደም አስፈላጊነት

  1. ከከንቱ ኑሮአችንም የተገዛነው እና የተዋጀነው በክርስቶስ ደም ነው፡፡
ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡18-19
  1. ከሞተ ስራ ህሊናችንን ያነፃው የክርስቶስ ደም ነው፡፡
ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን? ዕብራውያን 9፡14
ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤ ዕብራውያን 10፡22
  1. የተቀደስነው በክርስቶስ ደም ነው፡፡
ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ። ዕብራውያን 13፡12
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ሮሜ 3፡25
  1. የተቤዠነው በክርስቶስ ደም ነው፡፡ ካለደም ስርየት የለም፡፡
በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ኤፌሶን 1፡7
እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም። ዕብራውያን 9፡22
  1. የሃጢያት ልብሳችን የታጠበው በክርስቶስ ደም ነው፡፡
እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ። ራእይ 7፡14
ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ ራእይ 1፡5
  1. በእምነት በፀጋ ብቻ የምንፀድቅበት አዲስ ኪዳን የተሰጠን በክርስቶስ ደም በኩል ነው፡፡
እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። 1ኛ ቆሮንቶስ 11፡25
  1. የፀደቅነው በደሙ ነው፡፡
ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ሮሜ 5፡9
  1. ወደእግዚአብሄር የቀረብነው በክርስቶስ ደም ነው
አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። ኤፌሶን 2፡13
  1. የክርስቶስን ስጋ ያልበላ የክርስቶስን ደም ያልጠጣ በራሱ ህይወት የለውም፡፡
ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ዮሐንስ ወንጌል 6፡53
  1. የክርስቶስን ደም የናቀ ሌላ ምንም የመዳን እድል የለውም
የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? ዕብራውያን 10፡29
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ጠቦት #በግ #ደም #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

No comments:

Post a Comment