Popular Posts

Thursday, August 10, 2023

ልጆቻችንን ከተመሳይ ፆታ ተግዳሮት መጠበቅ ክፍል 3

 

ማንም ሌላ ሰው ስለተፈጥሮአዊው የፆታ ግንኙነት ግራ ቢጋባ እኛ ግራ አንጋባም፡፡

ስለእግዚአብሄር አፈጣጠር ንድፍ እና ዲዛይን ከምናውቅ ከእኛ  በላይ መፍራት የሌለበት እና በመተማመን መኖር ያለበት ሌላ ሰው የለም፡፡

ሰይጣን በአለም አማካኝነት የእግዚአብሔርን ዲዛይን በላጲስ ለማጥፋት ሲነሳ አለም እኛን እንደ ታላቅ እንቅፋት ትፈራናለች እንጂ እኛ አለምን አንፈራም፡፡

በእግዚአብሔር ቃል በመታጠቅ በድፍረት መኖር አለብን እንጂ መፍራት የለብንም፡፡ ማንም ቢፈራ እኛ ግን መፍራት የለብንም፡፡

ታዲያ የአለም ጥቃት ሲፈፀምብን ከተርበተበትን ልጆቻችን እኛ እውነት እንደሌለን ሊያስቡ ይችላሉ፡፡

ልጅ ወልደን ማሳደግ የጀመርነው አለም በክፉ ያልተያዘች ስላልሆነች አይደለም፡፡ ይልቁንም በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል ልጆችን ወልደን እግዚአብሔርን የሚፈራ ትውልድ ለእግዚአብሔር እናቀርባለን ብለን የተወራረድን ሰዎች ነን፡፡

እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? በሥጋም በመንፈስም የእርሱ ናቸው። ለምን አንድ አደረጋቸው? ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለውን ዘር ይፈልግ ስለ ነበር ነው። ሚልክያስ 2፡15

ልጆቻችንን ለመምራት ከእኛ በላይ ልጆቻችንን ለመምራት እ፡ድሉ ያለው ማንም የለም፡፡ ልጆቻችንን እየቀረብን ጓደኛ እያደረግናቸው ምንም ተግዳሮት ሲገጥማቸው እንዳይይደብቁን አድርገን ጓደኛ ማድረግ አለብን፡፡

ልጆቻችንን ከእኛ ምንም የማይደብቁ የቅርብ ጓደኞቻችን ካደረግናቸው በህይወታቸው የሚመጣውን ማንኛውንም የእኩዮሽ ግፊት እንዲያሸንፉ አብረናቸው በመቆም እንረዳቸዋለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር  #ግብረሰዶም #ግብረሰዶማዊነት


No comments:

Post a Comment