ይህም
የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤
አንድ
የሰማሁትን ልቤን የነካኝን ታሪክ ላካፍላችሁ፡፡
በክርስትያን
ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ልጅ ወደ ታላቅ እህቱ ይሄድና እግዚአብሄርን ማየት እፈልጋለሁ ይላታል፡፡ እህቱም አይደለም እኮ እግዚአብሄር
አይታይም ብላ ትመልስለታለች፡፡ በመልሱ ያልረካው ልጅ ወደ እናቱ ጋር ይሄድና እማዬ እንዴት ነው እግዚአብሄርን ላየው የምችለው ይላታል፡፡ እሱዋም እግዚአብሄር
የሚታየው በቃሉ ነው ብላ ትመልስለታለች፡፡ በእህቱም በእናቱም መልስ ያልረካው ልጅ በእርጅና ምክኒያት አይናቸው ወደፈዘዘ ወደአያቱ
ይቀርብና አያቴ እግዚአብሄርን ማየት እፈልጋለሁ ብዬ እህቴን ብጠይቃት እግዚአብሄር አይታይም አለችኝ እናቴ ደግሞ እግዚአብሄር በቃሉ
ነው እንጂ አይታይም አለችኝ፡፡ ፊታቸው በደስታ የበራው አያቱ ልጄ አሁን አሁንማ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ምንም ነገርም አልታይም
ብሎኛል አሉት ይባላል፡፡
በእነዚህ
መካከል የነበረው ልዩነት የእይታ ልዩነት ነው፡፡ ለአያትየው መንፈሳዊው አለም ፍንትው ብሎ ከመታየቱ የተነሳ የምድራዊው ነገር ጨልሞባቸዋል፡፡
ኢየሱስ ጌታና ንጉሷ የሆነባት የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችን አለች፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቱ እንደሞተለት አምኖ ዳግመኛ ያልተወለደ ማንም ሰው የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።ዮሐንስ 3፡3
ዳግመኛ እንደተወለድን እንደ
እኛ ባለጠጋ ሰው የለም፡፡ ግን ማየት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን አይናችን ተከፍቶ ካላየን ባለጠጋ ለመሆን በከንቱ በመድከም ጊዜያችንን
እናባክናለን፡፡
ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡18-19
የሰው ጤንነት አይን ነው፡፡ አይኑ የታመመና በትክክል የማያይ ሁለንተናው ይጨልማል፡፡
መዝገብህ
ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ! ማቴዎስ 6፡21-23
መንፈሳዊውን አለም ማየት የተሳናትን የቤተክርስትያን
መሪ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ ይላል ጌታ፡፡ ሰው ካላየ ደሃ ሆኖ ባለጠጋ ነኝ
ብሎ ይመካል ራቁቱን ሆኖ የዘነጠ ይመስለዋል፡፡
ባለ
ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ። ራእይ 3፡18
ይህም
የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ኤፌሶን 1፡18-19
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እይታ #አይን #ቃል #የጠራ #ኩል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment