ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፥ በረሀውም ሐሤት ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል። እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ። የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ። ፈሪ ልብ ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው። ትንቢተ ኢሳይያስ 35፡1-4
·
ምድረ በዳውና
ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፥
ምድረ በዳ የተጠማ ደረቅ ምድር ነው፡፡ የእግዚአብሄር ክንድ ሲመጣ ምድረበዳው በውሃ ይረሰርሳል፡፡ ውሃ በማጣት የደረቀውና
ህይወት ያጣው መሬት ህይወት ያገኛል፡፡
እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በራሱ ምክና እምሳለ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በክብሩ ነው፡፡ የሰው ጉስቁልና
የእግዚአብሄር ፈቃድ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በሰው መለምለም ፣ ማበብ ፣ መሳካትና መከናወን እንጂ እግዚአብሄር በሰው
ጉስቁልና አይደሰትም፡፡
·
በረሀውም ሐሤት
ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል
መሬት ለልምላሜ እና ለፍሬያማነት ሰለተሰራ ድርቀትና በረሃማነት መሬትን ያሰቃየዋል፡፡ ነገር ግን የእግአብሄር ክንድ
ሲገለጥ በረሃው ወደ ተፈጥሯዊ ደስታው ይመለሳል፡፡ ፅጌረዳም የሚያምርበት ሲጠወልግ ሲጎሳቆል ሳይሆን ሲለምልም አበባ ሲያወጣ ነው፡፡
·
እጅግ ያብባል
በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል
ፅጌረዳ እንዲያብብና እንዲያፈራ ስለተሰራ ፅጌረዳ ሲጠወልግና ሲከስም ደስ አይልም፡፡ ፅጌረዳ ሲያብብ ለራሱም ለሌሎችም
ደስታ ይሆናል፡፡
·
የሊባኖስ ክብር፥
የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል
የእግዚአብሄር ክብርን ግርማ እናያለን፡፡
·
የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም
ግርማ ያያሉ።
ይህ ሁሉ የእግዚአብሄር
ክብር በህይወታቸን መገለጥ የተስፋ ቃል በህይወታችን እንዲፈፀምና ሁላችንም አብረን እንድንወርስ ማድረግ ያለብንን ነገር ይናገራል፡፡
·
የደከሙትን እጆች
አበርቱ፥
ይህ የተስፋ ቃል እንደሚፈፀም
ማመን በሚገባ እንድንዘጋጅ ያደርገናል፡፡ ይህ ተስፋ ያለው ከእነዚህ ነገሮች ራሱን ያጠራል ይላል መፅሃፍ ቅዱስ፡፡
በእርሱም ይህን
ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፡3
·
የላሉትንም ጕልበቶች
አጽኑ።
በላላ ጉልበት ወደ
እግዚአብሄር ክብር ውስጥ መግባት አይቻልም፡፡ ስለዚህ የላሉትን ጉልበቶች አፅኑ፡፡
የአዋጅ ነጋሪ
ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡3-4
·
ፈሪ ልብ
ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው
አጽናኑ፥ ሕዝቤን
አጽናኑ ይላል አምላካችሁ። የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥
ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡1፣5
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ
#ክብር #ሃይል #ዘላለም #ጥበብ #የእግዚአብሄርመንግስት #ንጉስ #እርሾ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment