Popular Posts

Thursday, August 23, 2018

የአዲስ ዓመት ውሳኔ - ቀለል ያለ ህይወት መኖር

እግዚአብሄር አባታችን ነው ለእኛ ያስባል፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር እረኛችን ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚያስፈልገንን ሁሉ ያቀርብልናል፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙረ ዳዊት 23፡1
ህይወታችንን በሚያስፈልገን ነገር ላይ ከወሰንነው በሰላም እንኖራለን፡፡ ህይወታችንን በሚያስፈልገው ነገር ላይ ካልወሰነውና እኛ በምንፈልገው ነገር በባለጠግነት ምቾት ላይ ካተኮርን ህይወታችን ይወሳሰባል፡፡
በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። የሉቃስ ወንጌል 8፡14
እግዚአብሄር ሰውን ቀለል አድርጎ ፈጥሮታል፡፡ እግዚአብሄር ሰው ቀለል ብሎ እንዲኖር ይፈልጋል፡፡ ሰው እግዚአብሄር የሚያስፈልገውን እንደሚያሟላለት ካመነ ህይወቱ ቀለል ይላል፡፡ ሰው ህይወቱ ቀለል ካለ እና በመጠኑ ከኖረ ከራሱ አልፎ የተፈጠረበትን ሰዎችን የማገልገል አላማውን በምድር ላይ መፈፀም ይችላል፡፡
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። በመጠን ኑሩ ንቁም 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡7-8
ህይወቱ በሚያስፈልገው ነገር ላይ ያላተኮረ ሰው ህይወቱ ቀለል ሊል አይችልም፡፡ ህይወቱ ቀላል ካላለ ለእግዚአብሄር ፍሬያማነት ይቀንሳል፡፡ ህይወቱ ቀለል ያለ ሰው ብቻ ከራሱ አልፎ ሌሎችን ማገልገል ይችላል፡፡
ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡4
ሰው እግዚአብሄርን ለማገልገል ጊዜ ፣ ጉልበት ፣ አቅምና ገንዘብ የሚያገኘው ያለኝ ይበቃኛል ሲል ብቻ ነው፡፡ ያለኝ ይበቃኛል የማይልና ባለው ነገር የማይረካ ሰው መቼም የማይሞላ መፈለጉን ሲከተል ህይወቱን ያባክናል፡፡
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡6፣8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#መሰረታዊፍላጎት #ነፃነት #አትጨነቁ #ቅድሚያ #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ንቁ #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #የአለምሃሳብ #የባለጠግነትማታለል #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment