Popular Posts

Friday, August 17, 2018

እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል

የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡15
በህይወት ከሚያሳርፉ ነገሮች አንዱ መንፈሳዊ ነገር የእግዚአብሄርና የሰው ድርሻ እንዳለበት መረዳት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራው እኛ የማንሰራው ስራ አለ፡፡ እኛ የምንሰራው እግዚአብሄር የማይሰራው ስራ አለ፡፡  
መስራት የምንችለውንና መስራት የማንችለውን እንደማወቅ ሰላምን የሚሰጥ ነገር የለም፡፡ መስራት የምንችለውን ሰርተን መስራት የማልንችለውን ለመስራት ከመፍጨርጨር ማረፍን የሚሰለ ነፃነት የለም፡፡
በህይወት የእግዚአብሄርን ስራ መከተል ሰላምን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር በማይሰራበት ቦታ ለመስራት አለመሞከር ሰላምን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሄር አብሮን በማይሰራበት ቦታ ጉልበትን አለማባከን ጥበብ ነው፡፡
የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡9
በህይወት እኛ መስራት የምንችለው ነገር አለ፡፡ በህይወት እኛ መስራት የማንችለው ነገር አለ፡፡ በእኛ ውሳኔ ላይ የሚደገፍ ነገር አለ፡፡ በህይወት ደግሞ በእኛ ውሳኔ ላይ የማይደገፍ ነገር አለ፡፡ ስለራሳችን ውሳኔ እንጂ ነፃ ፈቃድ ስላለው ስለሌላው ሰው ውሳኔ እኛ ሃላፊነት መውሰድ አንችልም፡፡  
ከዚህ አንፃር በእኛ ውሳኔ ላይ በማይደገፍ ነገር ላይ ጉልበትን መጨረስ ሞኝነት ነው፡፡ በእኛ ውሳኔ ላይ የሚደገፈውን ነገር ሁሉ አድርገን ሌላውን ለእግዚአብሄር መተውን የመሰለ ሰላምን የሚሰጥ ነገር የለም፡፡
እግዚአብሄር እንድንከተለውና እንድናገለግልው የሚፈልገው በሰላም ነው፡፡ በሰላም እንጂ በፍርሃት እንድናገለግለው እግዚአብሄር አልጠራንም፡፡
በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን። የሉቃስ ወንጌል 1፡74-75
እግዚአብሄር ማድረግ የምንችለው ነገር አድርገን በሰላም እንድንኖር ጠርቶናል፡፡ እግዚአብሄር ማድረግ የማንችለውን ነገር ለማድረግ በመሞከር እንድንሰቃይ አልጠራንም፡፡ እግዚአብሄር ግን በሰላም ጠርቶናል፡፡
የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡15
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አእምሮ #መንፈስ #ሰላም #ልብ #ድርሻ #አብረን #ድንበር #ጥሪ #አይታወክ #አይፍራ #ጭንቀት #ቅባት #ይግዛ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment