Popular Posts

Monday, August 6, 2018

የሚነቅፈው ነገር ካለው

እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡13
ሰውን ይቅር እንደማለት የሚፈታ ነገር የለም፡፡ ሰውን ይቅር እንደማለይ ነፃ የሚያደርግ ነገር የለም፡፡
ሰው ላይ እንደመያዝ የሚያስርና የሚያሰቃይ ነገር የለም፡፡ ሰው ላይ እንደመያዝ ነፃነትን የሚነፍግ ነገር የለም፡፡ ሰው ላይ ሃጢያቱን እንደመያዝ የሚያሰቃይ ነገር የለም፡፡
የሰውን ነቀፋ ከመያዝ የሚቀድመው ሲጀመር ከእኛ የተለየውን ሰው መታገስ ነው፡፡ ትእግስት ማድረግ በሰው ላይ ይዘን ይቅር ከማለት ይለያል፡፡ ትእግስት ማድረግ ማለት ሰው የበደለንን ነገር ይዘነው ይቅር ማለት አይደለም፡፡ ትእግስት ማድረግ ሰው ቢበድለን እንኳን እንደማንይዝበት አስቀድሞ መወሰን ነው፡፡ ትእግስት ማድረግ ማለት ሰው ሲበድለን ሲጀመር አለመያዝ ነው፡፡  
ሰውን ይቅር ማለት መልካም ነው፡፡ የሰውን በደል ይዞ ሰውን ይቅር ማለት አስፈላጊ ነው፡ሰው ይቅር ለማለት እንጂ በደልን ለመያዝ አልተፈጠረም፡፡ ሰው ሰውን ለመታገስ እንጂ በደልን እንዲይዝ አልተፈጠረም፡፡ ሰው ሰውን ታግሶ አብሮ እንዲኖር እንጂ ለሰው የክፋት ምላሽ እንዲሰጥ አልተፈጠረም፡፡  
በሰው ላይ ሲጀመር በደለን አለመያዝ ይቅር ከማለትም ይበልጣል፡፡ ሰው ላይ በደል ይዞ ይቅር ማለት ይብዛም ይነስም በደሉን የያዘውን ሰው የሚጎዳው ነገር አለ፡፡ ሰው በሰው ላይ በደልን ይዞ ይቅር እስከሚል ድረስ ባለው ጊዜ ይጎዳል፡፡ ሰው በደልን በሚይዝበትና በደልን ይቅር በሚልበት መካከል ነፃነቱን ያጣል፡፡ ሰው በሚበደልበትና በደሉን በሚተውበት መካከል ይሰቃያል፡፡
እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው። የማቴዎስ ወንጌል 18፡33-34
ሰው ቢቻል ቢታገስ መልካም ነው፡፡ ባይቻል ደግሞ በፍጥነት ይቅር ማለት በፍጥነት ነፃነቱን ይሰጠዋል፡፡ ሰው በደለን በያዘ መጠን እየተጎዳ ይሄዳል፡፡ ሰው ከሰው ጋር ባለው ግንኙነት በደልን በያዘ መጠን ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት እየተዛባ ይመጣል፡፡
ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። የማቴዎስ ወንጌል 6፡14-15
በሰው ላይ በደልን መያዝ በዳዩን ከሚጎዳው በላይ ተበዳዩን ይጎዳል፡፡  ከሚጎዳው በላይ ተበዳዩ ይጠቀማል፡፡ በሰው ላይ በደለን አለመያዝ ከበዳዩ በላይ ተበዳዩን ይጠቅማል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ይቅርታ #ምህረት #ፍርድ #ጠላት #ዲያቢሎስ #ስፍራ #ኢየሱስ #ጥላቻ #ትእቢት #መራርነት #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment